ኢትዮጵያ እና አልጄሪያ በወንጀልና ፍትሐብሔር ጉዳዮች ላይ ትብብር ለማድረግ የሚያስችሏቸዉን ስምምነቶች ተፈራረሙ

Ethiopia And Algeria Signed Agreements To Cooperate On Criminal And Civil Matters

በኢትዮጵያ እና በአልጄሪያ መንግስታት መካከል የወንጀልና ፍትሐብሔር ጉዳዮች ላይ ድርድራቸዉ የተጠናቀቁ ሶስት የሁለትዮሽ ስምምነቶች እንዲሁም በሁለት የፍትሕ ሚኒስቴሮች መካከል በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ የፊርማ ስነ-ሥርዓት መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም በሁለቱ አገራት የፍትሕ ሚኒስትሮች በኩል ተካሂዷል።

የፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ በዋናነት በሁለቱ አገራት መንግስታት መካከል በወንጀል እና ፍትሐብሔር ጉዳዮች የጋራ የሕግ ትብብር ለማድረግ የሚያስችሉ በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የሕግ ትብብር ፣ በፍትሐብሔር እና ንግድ ጉዳዮች የጋራ የሕግ ትብብር እንዲሁም በወንጀል የሚፈለጉ ግለሰቦችን አሳልፎ መስጠት ስምምነቶች ላይ መግባባት ላይ መደረሱን ተከትሎ የተደረገ ሲሆን፣ በተጨማሪም የሁለቱ አገራት የፍትሕ ሚኒስቴሮች መካከል ተቋማዊ ትብብር እንዲኖር የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድም ተፈራርመዋል።

ከፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ጎን ለጎን በሁለቱ ሀገራት የፍትሕ ሚኒስትሮች መካከል የሁለትዮሽ ውይይት የተደረገ ሲሆን በውይይቱም ኢትየጵያ እና አልጀሪያ በኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለረዥም አመታት የቆየ ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸዉ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህንኑ ግንኙነት የበለጠ አጠናክሮ ለማስቀጠል በዛሬዉ ዕለት በሁለቱ አገራት መካከል የተደረሰው ስምምነት በአገራቱ መካከል ተቋማዊ እና መደበኛ አሰራር የበለጠ እንዲጠናከር ላቅ ያለ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።

ከዚህም ባሻገር በዛሬዉ ዕለት ስምምነት ከተደረሰባቸዉ ጉዳዮች በተጨማሪ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን፣ ሽብርተኝነትን፣ የሀብት ማሰመለስ እንዲሁም የግልግል ዳኝነትን በተመለከተ በቀጣይ በጋራ ለመስራት ፅኑ ፍላጎት እንዳላቸዉ የተገለፀ ሲሆን ዛሬ የተፈረሙት ስምምነቶችም በቀጣይ ለሚኖሩ የጋራ ስራዎች አጋዥ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ልዩ ትኩረት ሰጥታ እየሰራችበት ባለዉ የዲጅታላይዜሽን ዘርፍ ላይ ልምድ ልዉዉጥ ለማድረግ ሁለቱ አገራት ተቀራርበዉ እንደሚሰሩም ተገልጿል።

የፍትሕ ሚኒስትሮቹ በዛሬዉ እለት የተፈረሙት ስምምነቶች በተቋማቱ መካከል ያለዉን ግንኙነት የበለጠ አጠናክሮ ለማስቀጠል አጋዥ እንደሚሆኑ እንዲሁም ሕግ እና ፍትሕን ጨምሮ በሌሎች ዘርፎች ላይ በሁለቱ አገራት መካከል ለሚኖረው ሁለንተናዊ ግንኙነት እንደ መነሻ እንደሚያገለግሉ ያላቸዉን እምነት ገልጸዋል፡፡

የስምምነቶቹ የፊርማ ስነ ሥርዓት መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሐና አርዓያስላሴ እና በአልጄሪያ የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ሉጥፊ ቡጁሙዓ አማካኝነት ተከናዉኗል፡፡

Tagged Under: 1994 agreement 1996 agreement 1996 criminal code agreement agreements algeria and healthcare administration and control authority charge civil civil and political rights civil matters Crime criminal criminal matters ethiopia revenue and customs authority illegal act international convention on civil and political rights international covenant on civil and political rights legal assistance in criminal matters matters medicine and healthcare administration and control authority medicine and healthcare administration and control proclamation no. 661/2009 offense per rate technical and vocational education and training technical and vocational education and training (tvet) violation
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች