በፍትሕ ሚኒስቴር የ2018 መጀት ዓመት የ6ወር ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ

Ministry of Justice Evaluates 6-Month Plan Implementation for 2018 Fiscal Year

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፍትሕ ሚኒስቴር የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድን መሰረት በማድረግ የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀምን የተቋሙ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም ሰራተኞች በተገኙበት ጥር 18/2018 ዓ.ም ገምግሟል፡፡

በግምገማ መድረኩ በዋናነት በማኅበረሰብ ፍትሕ አገልግሎት፤በነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት፤በንቃተ-ሕግ ሽፋንና ተደራሽነት፤በጥብቅና ፈቃድ እድሳት አገልግሎት፤የህግ ጥናት፣ማርቀቅና ምክርን በተመለከተ፤የሕግ ምርመራ/እርማትን በተመለከተ፤በወንጀል ምርመራና ክስ፤ በድርድር የሚፈቱ የፍትሐብሔር ጉዳዮች፤የሕግ ተፈጻሚነትና ተገዢነት ክትትል ጉዳዮች ጋር ተያይዞ በበጀት ዓመቱ 6ወራት ውስጥ የተከናወኑ ተግባራትን ለመገምገም የሚያስችል ሪፖርት ቀርቧል፡፡

በሪፖርቱ እንደተመላከተው በህግ እና ፍትሕ ማሻሻያ ስራዎች በኩል በርካታ ሃገራዊ እድምታ ያላቸው የሕግ ጥናቶች እና የሕግ ማርቀቅ ተግባራት መከናወናቸው እና በፍትሐብሄር ጉዳይ እንዲሁ የመንግስት እና የህዝብ ጥቅምን በማስጠበቅ ረገድ የላቀ ውጤት የተመዘገበ ሲሆን፣ ለሴቶች ሕፃናት አካል ጉዳተኞች እና ለተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች የህግ ምክር እንዲሁም ነፃ የህግ ድጋፍ አገልግሎት መሰጠት መቻሉ ተገልጿል፡፡

የወንጀል ፍትሕ አስተዳደርን በተመለከተ እንዲሁ ከፌደራል እና አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ መሰረት የምርመራ ስራዎችን በጋራ በመስራት የምርመራ ጥራት እና ቅልጥፍናን ለማሻሻል የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ ከመሆኑ በተጨማሪ የወንጀል መዛግብት ማጥራት እና የክርክር መዝገብ የመርታት ምጣኔን በእቅድ መሰረት መከወን መቻሉ ተመላክቷል፡፡

በሕዝብ እና በመንግስት ጥቅም ላይ በተፈፀሙ ከባድ ወንጀሎች የተመዘበሩ የህዝብ እና የመንግስት ሀብቶችን በማስመለስ ረገድ አበረታች ስራዎች መከናወናቸው በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡

በአጠቃላይ በሁሉም ዘርፎች እንደ ተቋም አበረታች የሆኑ ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን፤ በቀጣይም የፍትሕ አገልግሎት አሰጣጡን በተማከለ መልኩ ወደ ሥራ የማስገባት፤ አማራጭ የሙግት መፍቻ ስርዓትን በአደረጃጃት የመደገፍ ስራዎች፤ የህግ የበላይነትን የማክበር እና የማስከበር ሥራ፤ በረቂቅ ደረጃ ያሉ የቆዩ ህጎችን የማፀደቅ፤ ቅንጅታዊ አሰራሮችን የመዘርጋትና አጠናክሮ የማስቀጠል፤ የአስተዳደር ፍትህ ሂደቱን የመፈተሽ፤ በማረምና ማነፅ ሂደት የተለዩ ግኝቶችን የመፍታት፤ ተቋማዊ አቅምን በአዲስ አደራጃጀቶች እና በሰው ሃይል የማጠናከር ሥራዎች ላይ ከተቋም በዘለለ ሀገራዊ ዕይታን በማከል ትኩረት ተደርጎ ሊሰራ እንደሚገባ በበላይ አመራሩ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡

Tagged Under: 1990 Fiscal Year • 2015 fiscal year • appropriation • Budget • budget year plan • duty • Economic • ethiopian federal ministry of justice • Ethiopian Ministry of Justice • fdre ministry of justice • federal ministry of justice • finance • financial • fiscal • Fiscal Year • fiscal year 1990 • fiscal year 1991 • fiscal year 2000 • Implementation • Justice • ministry • plan • plan implementation • Revenue • spending • Tax • taxation • year
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች