የአልጀሪያው የፍትሕ ሚኒስቴር ክቡር ሚኒስትር እና የልዑክ ቡድናቸው ለ2 ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
የልዑክ ቡድኑ አዲስ አበባ ቦሌ አየር መንገድ ሲደርስ የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ በላይሁን ይርጋ አቀባበል አደርገውላቸዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ በቆይታቸው ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ጋር በተለያዩ ሕግ ነክ ጉዳዮች እና ትብብሮች ላይ ውይይት ያደርጋሉ። ከዚህ በተጫማሪም ክቡር ሚኒስትሩ ከፌደራል ከጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ከማረሚያ ቤት ኮሚሽን እና ከፌዴራል ሕግና ፍትሕ ምርምር ኢንስቲትዩት አመራሮች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።