በፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ፍቃዱ ፀጋ ከህዳር 25 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የሕግ አማካሪ ሆነው የተሾሙ ሲሆን፤ አቶ ተስፋዬ ዳባ ደግሞ ከህዳር 25 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሹመዋል፡፡
ይህን መነሻ በማድረግ ህዳር 27 ቀን 2016 ዓ.ም በሁለቱ ከፍተኛ አመራሮች መካከል የስራ ርክክብ ተደርጓል፡፡