በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ህግ ዳይሬክቶሬት እና በፍትሕ ሚኒስቴር የሴቶችና የባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የ2015 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አቀረቡ

Women and Children Affairs Public Prosecution Directorate and Ministry of Justice Women and Multi-Sectoral Affairs Directorate Present 2015 EC Performance Reports

ሴቶች እና ሕፃናትን አስመልክቶ በክልሎች እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ላይ ሰኔ 8 ቀን 2ዐ15 ዓ.ም. የተጀመረው የውይይት መድረክ ቀጥሎ በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት እና በፍትሕ ሚኒስቴር የሴቶችና የባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የ2015 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም ሪፖርቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት በጾታቸው ወይም በዕድሜአቸው ምክንያት ለወንጀል ጥቃት ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚፈፀምባቸውን ወንጀል የምርመራ ሆነ የክርክር ስራዎችን በመከታተል በማስተባበርና ድጋፍ በመስጠት ወንጀል ፈፃሚዎች ሕግ ፊት ቀርበው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙና ሌሎችም እንዲማሩ በማድረግ የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ጥረት እያደረገ መሆኑን በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ፅጌ የማነ ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት ገልፀዋል፡፡

በዳይሬክቶሬቱም ሆነ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ሴቶች እና ሕፃናትን በሚመለከት በክርክር ውሳኔ ካገኙ 261 መዛግብት ውስጥ 251 መዛግብት እንደ ወንጀሉ ሁኔታ የቅጣት ውሳኔ ያገኙ መሆኑም በቀረበው ሪፖርት ተካቷል፡፡

በፍትሕ ሚኒስቴር የሴቶችና የባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በበኩለ ሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፍጸሙ ጥቃቶችን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የተቋቋመውን ብሔራዊ አስተባባሪ አካል ማስተባበር ፣የፍትሕና እንክብካቤ ማዕከላት ክትትልና ድጋፍ ማደረግ ፤በክልሎች የፍትሕና እንክብካቤ ማእከላት እንዲደራጁ ድጋፍ መስጠት ፣ሴቶች፣ ሕፃናት፣ ወጣቶች እና ባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮችን አስመልክቶ የወጡ ህጐች እና አሠራሮች ዙሪያ የታዩ ክፍተቶች እና አዲስ በሚወጡት ህጐች ላይ አስተያየት ማቅረብ ፣ተቋማት ለሚያቀረቡት የሕግ ድጋፍ እና ሌሎች ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት በተቋሙ ሁሉም የስራ ክፍሎች የሴቶች፣ ሕፃናትና ባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮችን አካተው እዲተገበሩ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን በዳይሬክቶሬቱ ዐቃቤ ሕግ የሆኑት እመቤት ጌታቸው ገልፀዋል፡፡

በፌደራልም ሆነ በክልሎች በሴቶች እና ሕፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን የሚከታተሉ መዋቅሮች ተመሳሳይ አደረጃጀቶች እንዲኖራቸው፣ በዚህ አደረጃጀት የሚጣሩ የወንጀል አይነቶችን ወጥ ማድረግ እንዲሁም የምርመራ እና የክስ ሂደቶችን በበቂ የባለሙያ ስብጥር እንዲደራጁ ማድረግ እንደሚያስፈልግ የገለጹት በፍትሕ ሚኒስቴር የሴቶች እና ባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ዳግማዊት አለምኔ የመረጃ አያያዝ እና ቅንጂታዊ አሠራር በልዩ ትኩረት ሊሰራባቸው እንደሚገባም በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡

በተቋማት መካከል ያለ ቅንጅት ደካማ መሆን በሁሉም ክልሎች ላይ እንደ ችግር የተነሳ በመሆኑ በአገር ደረጃ ወጥ አፈጻጻም እንዲኖር ለማደረግ ሁላችንም የበኩላችንን አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚያስፈልግ ወ/ሮ ዳግማዊት አለምኔ አመላክተዋል፡፡

በመጨረሻም ለቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ለ2 ቀናት የተካሄደው ውይይት ተጠናቋል፡፡

Tagged Under: abuse • Capacity Building • case management • charge • child • Child Abuse • children • Crime • criminal • Criminal Investigation • data management • gender-based • Gender-Based Violence • illegal act • Justice • Legal Frameworks • offense • performance • Performance Report • Prosecution • public • public prosecution • report • Sentencing • violation • violence • women
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች