የአፍሪካ የአለምአቀፍ ህግ ማህበር 12ኛ አመታዊ ስብሰባ በአዲስ አበባ ተካሄደ

The 12th Annual Conference of the African Society of International Law Held in Addis Ababa

የአፍሪካ የአለምአቀፍ ሕግ ማህበር 12ኛ አመታዊ ስብሰባ በአዲስ አበባ ጥቅምት 16 እና 17 ቀን 2016 ዓ/ም አፍሪካ እና የአለም የጋራ ሀብቶች አስተዳደር በሚል ርዕስ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

በአመታዊ ስብሰባው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኤርሚያስ የማነብርሃን ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የአለም የጋራ ሀብቶች (global commons) ባህር፣ አትሞስፌር፣ የአለም ዋልታዎች እና ጠፈር በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው ብለዋል፡፡ ዶ/ር ኤርሚያስ አያይዘውም እነዚህ የጋራ ሀብቶች የሰው ልጆች ሁሉ የጋራ ቅርስ (common heritage of mankind) ተደርገው እንደሚወሰዱ ገልጸው ዘላቂ ጥበቃ እና አስተዳደር ብሎም ተደራሽነት እና ህጋዊ ተጠቃሚነት ላይ በትብብር እና በቅንጅት በአፋጣኝ መሥራት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡

በስብሰባው ላይ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ የውጭ ሀገር እና የሀገር ውስጥ የአለምአቀፍ ሕግ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን በታዋቂ የአለምአቀፍ ሕግ ባለሙያዎች በርካታ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ የማህበሩ ፕሬዚዳንት የሆኑት ፕሮፌሰር ማካን ምቤንግዌ ለአመታዊ ስብሰባው መሳካት አስተዋፅኦ ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል፡፡

Tagged Under: ababa addis addis ababa african African Society of International Law annual common common heritage of mankind commons conference dr. ermias yemaneberhan global Global Commons heritage international International law law Legal Reform outer space polar regions resource access society
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች