የዓለም ዓቀፍ ሕጎችን ተላልፈው በሚፈፀሙ ወንጀሎች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሥልጠና እየተሰጠ ነው

Training Kicks Off on Crimes Breaching International Law


በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ፣ ትምህርት እና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት ከዓለም ዓቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ጋር በመተባበር የዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊነት ሕግ ተላልፈው በሚፈፀሙ ወንጀሎች እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሥልጠና ከዛሬ ነሐሴ 2ዐ-22 ቀን 2ዐ17 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡
ሥልጠናው በዋናነት በዘርፉ የሚሰሩ ዐቃቢያነ ሕግ አዲስ እውቀትና ክህሎት እንዲያገኙ፣ ቀደም ሲል የነበራቸውን እውቀት ለማዳበር እና በሥራ ያካበቷቸው ልምዶች ልውውጥ ለማድረግ እንደሚያግዛቸው የተገለፀ ሲሆን በተለይም ከዚህ ቀደም በዘርፉ ረጅም ጊዜ ሲሰሩ የነበሩ ዐቃቢያነ ሕግ ያላቸውን ተጨባጭ ልምድ የሚያካፍሉ ይሆናል።
ሥልጠናው በሶስት ቀናት ቆይታው የዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊነት ሕግ ምንነትና ጠቀሜታ፣ ሌሎች ዓለም ዓቀፍና አገራዊ የሕግ ማዕቀፎች፣ እነዚህን ወንጀሎች በመዳኘት በኩል የፍርድ ቤቶች ሚና፣ የጦር ወንጀል በኢትዮጵያ ሕግ፣ የፀረ-ሽብር ሕግ ከሰብአዊነት ሕግ ጋር ያለው እይታ የሚሉና እነዚህን ወንጀሎች በመመርመር በኩል የዐቃብያነ ሕግ ሚናና ዓለም ዓቀፍ ተሞክሮ የሚሉና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ይዳሰሱበታል።
በዚህ ሥልጠና በተቋሙ ከተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ጄነራል፣ ከድሬድዋ፣ ከሀዋሳ እና ከአዲስ አበባ የፍትሕ ሚኒስቴር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች የተውጣጡ ዐቃቢያነ ሕግ እየተሳተፉ ሲሆን ሥልጠናውም ልዩ የክረምት ሥልጠና ተብለው በተቋሙ አሥተዳደር ከተለዩ ስምንት ሥልጠናዎች ውስጥ የሚካተትና ሶስተኛው ሲሆን ሌሎች ሥልጠናዎችም በቀጣይ ቀሪ የሥልጠና መርሐ ግብሮች መሠረት ጊዜያቸውን ጠብቀው እንደሚሰጡ ተጠቁሟል፡፡

Tagged Under: academic act breach Capacity Building charge Charter constitution court Crime Crimes criminal decree directive Education fundamental law international International law judicial judiciary law learning legislation National Policy proclamation rea Regulation school statute Training
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች