የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴዔታ አቶ በላይሁን ይርጋ በኢትዮጵያ የኮሎምቢያ አምባሳደር ጋር ውይይት አካሄዱ

የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴዔታ አቶ በላይሁን ይርጋ በኢትዮጵያ የኮሎምቢያ አምባሳደር ጋር ውይይት አካሄዱ • State Minister of Justice Ato Belayhun Yirga held talks with the Ambassador of Colombia to Ethiopia

የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴዔታ አቶ በላይሁን ይርጋ በኢትዮጵያ የኮሎምቢያ አምባሳደር ከሆኑት ይሶን አርካዲዮ ጋር በሰላም እና ፍትሕ ዙሪያ ኢትዮጵያ እና ኮሎምቢያ በጋራ በሚሰሩበት ሁኔታ ዙሪያ ምክክር አድርገዋል፡፡

ኃላፊዎቹ ባደረጉት ውይይት ሁለቱ አገራት ከሽግግር ፍትሕ አንጻር የሚለዋወጡት ልምድ መኖሩን ገልጸው በጥናት እና ምርምር፣ በዓለም ዓቀፍ እና የባለድርሻ አካላት ምክክር መድረኮች አማካኝነት የእውቀት እና ልምድ ልውውጥ ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡

በሁለቱ ዓገራት የሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በጋራ ለመሥራት የሚችሉበትን ሁኔታ ለመፍጠር በኢትዮጵያ በኩል የኢትዮጵያ የሕግ ትምህርት ቤቶች ማህበር ከኤምባሲው ጋር አብሮ መሥራት መጀመሩ የተጠቀሰ ሲሆን ፍትሕ ሚኒስቴርም የሽግግር ፍትሕ ትግበራ ምዕራፍ አስተባባሪ እንደመሆኑ መጠን በትምህርት ተቋማቱ መካከል የሚደረገውን የትብብር ስራ በማስተባበር ሚናውን እንዲያበርክትም ተጠይቋል፡፡

በቀጣይ ሁለቱ አገራት በመካከላቸው ቋሚ እና ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር በሕግ እና ፍትሕ እንዲሁም በሰላም ማጽናት ዙሪያ በትብብር ለመሥራት የሚያስችሉ የመግባቢያ ሰነዶችን በመፈራረም ለተፈጻሚነቱ የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ አረጋግጠዋል፡፡

በመድረኩ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የደቡብ አሜሪካ እና ካሪቢያ አገራት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደምሰው ከበደ ተገኝተዋል፡፡

Tagged Under: Access to Justice addis ababa justice bureau administrative justice african charter on the rights and welfare of the child ambassador Amhara Regional State ato ato belayhun yirga belaineh yirga belayhun belayhun yirga beliyhun yirga Bilateral Talks central bank of ethiopia constitution of the federal democratic republic of ethiopia Convention on the Rights of the Child convention on the rights of the child (crc) Justice Justice For All - PF Ethiopia justice for all prison fellowship ethiopia minister minister of justice minister of state south west ethiopia peoples' regional state state state minister state minister of justice un un convention on the rights of the child yirga
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች