የሁሉም ክልሎች ፍትሕ ቢሮዎች ሀላፊዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲተገበር ታስቦ በተዘጋጀው የፍትሕ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ ተመርኩዘው የክልሉን የዕቅድ ዝግጅት አስመልክተው ማብራሪያ አቅርበዋል።
የክልል ፍትሕ ቢሮዎቹ ባቀረቡት የፍትሕ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ከሕግ፣ ከአደረጃጀት እና ከመሰረተ ማኅበረሰብ ፍትሕ አገልግሎት ረገድ እንዲሁም ባለሙያን ከማብቃት እና የሕዝቡን ንቃተ ሕግ ትምህርት ከማስፋት አንጻር በአጭር እና በረጅም ጊዜ ለማሳካት የተያዙ ዕቅዶች ተካተዋል።
በቀረቡት ዕቅዶች ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ውይይቱን የመንግሥት ሕግ እና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው እና የተቋም ግንባታ እና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኤርሚያስ የማነብርሀን መርተዋል።
ክልሎቹ ካቀረቡት ዕቅድ በመነሳት በቀጣይ ሶስት አመታት የፍትሕ ትራንስፎርሜሽን እቅዱን ለማስተግበር የሚያስችል ዝርዝር እቅዶች መዘጋጀቱን እንደ መልካም አጋጣሚ በመውሰድ ለተፈጻሚነቱ ሁላችንም የበኩላችንን ሚና ልንጫወት ይገባል፤ ፍትሕ ሚኒስቴርም ለዕቅዱ ተፈጻሚነት ተገቢውን ድጋፍ ያደርጋል ተብሏል።
በዚህ ወቅት መድረኩን በመልዕክታቸው እና በሰጡት የስራ አቅጣጫ ያስተላለፉትን መልዕክት ማጋራታችን ይታወሳል።