"የተሻለ ፍትህ ለህዝባችን" በሚል መሪ ቃል የተጀመረው ህዝባዊ መድረክ በሀዋሳ ከተማ ተካሄደ

Public Forum Launched Under the Motto "Better Justice for Our People" Held in Hawassa City

የፌዴራል ድጋፍ ሰጪ ቡድን አባላት በሲዳማ ክልል የፍትሕ ትራንስፎርሜሽን መድረክ ላይ በመገኘት ክልሉ ለፍትሕ ስርዓቱ መሻሻል እያደረገ የሚገኘውን እንቅስቃሴ አበረታተዋል።

የፍትሕ መሻሻልና ተደራሽነት መስፈን ከህብረተሰቡ ለሚነሱ የመልካም አስተዳደር እና ፍትሕ ጥያቄዎች በተገቢው በመመለስ ህብረተሰብን ከተለያዩ እንግልት ለመታደግ ፍትሕን ትራንስፎርም ለማድረግ ታስቦ በፍትሕ አካላት የተጀመረው ህዝባዊ መድረክ በሃዋሳ ከተማ ተካሂዷል።

የፌዴራል ሱፐርቪዥን ቡድን መሪ እና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ተስፋዬ ዳባ በጉብኝት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ፍትሕ በእጅ መንሻ እንዳይገዛ እና የፍትሕን ትራንስፎርሜሽን የተሳካ ለማድረግ ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦችን እንዲሰጡ አሳስበዋል።

ሚኒስቴር ዴኤታው አክለውም ባህላዊ የዳኝነት ስርዓት በሲዳማ አካባቢ ያለው የዳበረ እንዲሆን በማድረግ በቀላል ጉዳይ ሕዝብ ሳይጉላላ በየአካባቢው መፍትሄ ማግኘት እንዲችል የተጀመሩ ስራዎች ማጠናከር የሚያስችል አጋዥ ሀሳብ በማከል ውይይቱን ማድረግ እምነታቸው እንደሆን ጠቁመዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች ለፍትሕ መቀላጠፍ ችግር ናቸው ያሉትን ሀሳብ በሰፊው አንስተውና ተወያይተው መድረኩ ተጠናቋል።

በመድረኩ ላይ የክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ክብርት ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደ፣ የክልሉ ምክር ቤት አመራሮች እና የፍትሕ ዘርፍ ተቋማት ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን ዋና አፈ ጉባዔዋ ህዝባዊ መድረኩን መርተዋል። በመድረኩ የፌዴራል ክትትል እና የሱፐርቪዥን ቡድን አባላት በመገኘት ጉብኝት በማድረግ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሲዳማ ክልል

መጋቢት 13/2016 ዓ.ም

ሀዋሳ

Tagged Under: access • Access to Justice • city • federal • Federal Government • Forum • good • Good Governance • governance • Government • hawassa • hawassa city • judicial • judicial transformation • Justice • Justice Reform • Legal Reform • public • reform • region • regional council • Rule of Law • sidamo • sidamo region • Stakeholder Engagement • supervisory team • transformation
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች