የፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት ከሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት ውስጥ ትምህርትና ሥልጠና መስጠት ሲሆን የስራ ክፍሉ ፍላጎትን መሠረት ያደረገ ሥልጠና በማዘጋጀት ለተቋሙ ሰራተኞች እየሰጠ ይገኛል፡፡
የሥልጠናው ዓላማም የአይነ ስውራን ዐቃብያነ ሕግ ስራን ቀላልና በቴክኖሎጂ የተታገዘ ለማድረግ እንዲሁም አይነስውር ዓቃብያነ ሕግ ኪቦርድን መሠረት ያደረጉ መሠረታዊ የኮምፒውተር ክህሎታቸውን ከፍ ለማድረግ እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ችሎታቸውን ለማሳደግ ያለመ ሥልጠና መሆኑን የንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት የምክትል ሃላፊ ተወካይና የንቃተ ሕግ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ተክለ ልብሰወርቅ በመክፈቻ ንግግራቸው ገልጸዋል።
ሥልጠናውን የሰጡት ጠበቃና የሕግ አማካሪ የሆኑት አቶ ይልቃል ሀሳቤ እንደገጹት ይህ ሥልጠና መሠረታዊ የኮምፒውተር ሥልጠናን በተለይም ወርድ እና ኤክኤል አጠቃቀም ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን አውስተዋል፡፡ በተያያዘም ሰልጣኝ ዐቃብያነ ሕግም በበኩላቸው የተሰጣቸው ሥልጠና በነበራቸው እውቀት ላይ ተጨማሪ ነገሮችን ያገኙበት በመሆኑ በቀጣይ ስራዎቻቸው ላይ ከፍተኛ የሆነ እገዛ የሚያደርግላቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ይህ ሥልጠና በቀጣይም በተመሳሳይ መልኩ የሚሰጥ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡