የፍትሕ ሚኒስቴርን የኮሚዩኒኬሽን ስራዎች ለማሻሻል በሚያስችሉ ሁኔታዎች ዙሪያ ከአውሮፓ ህብረት የቴክኒካል ቡድን አባላት ጋር ውይይት ተካሄደ

Ministry of Justice Holds Discussions with EU Technical Team to Enhance Communication Activities

በፍትሕ ሚኒስቴር የፍትሕ ስርዓት ማሻሻያ እና ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት እና የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በጋራ በመሆን ከአውሮፓ ህብረት የቴክኒካል ድጋፍ ቡድን አባላት ጋር የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሚዩኒኬሽን ስራዎች ለማሻሻል በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል፡፡ በውይይቱም ፍትሕ ሚኒስቴር አሁን በተጨባጭ የሚገኝበትን የተግባቦት ደረጃ አስመልክቶ ገለጻ የተደረገ ሲሆን የድጋፍ ቡድኑ እገዛ ሊያደርግባቸው በሚችልባቸው ጉዳዮች ላይም ሃሳቦች ተነስተው ውጤታማ ውይይት ተደርጓል፡፡

የድጋፍ ቡድኑ አባላትም በሁለቱ ዳይሬክተሮች አቶ አወል ሱልጣን እና አቶ ኖህ ታከለ ከቀረላቸው ማብራሪዎች በመነሳት ድጋፍ ስለሚያደርጉባቸው የትኩረት መስኮች ተገቢውን መረጃ መያዝ መቻላቸውን ገልጸው የተቋሙን ተጨባጭ ሁኔታ ከሌሎች ሀገራት ልምዶች ጋር በማጣጣም የተቋሙን የተግባቦት ስራ ደረጃ ከፍታ ለመጨመር የሚያስችሉ ድጋፎችን እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

Tagged Under: Technical Assistance
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች