በፍትሕ ሚኒስቴር የፍትሕ ስርዓት ማሻሻያ እና ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት እና የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በጋራ በመሆን ከአውሮፓ ህብረት የቴክኒካል ድጋፍ ቡድን አባላት ጋር የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሚዩኒኬሽን ስራዎች ለማሻሻል በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል፡፡ በውይይቱም ፍትሕ ሚኒስቴር አሁን በተጨባጭ የሚገኝበትን የተግባቦት ደረጃ አስመልክቶ ገለጻ የተደረገ ሲሆን የድጋፍ ቡድኑ እገዛ ሊያደርግባቸው በሚችልባቸው ጉዳዮች ላይም ሃሳቦች ተነስተው ውጤታማ ውይይት ተደርጓል፡፡
የድጋፍ ቡድኑ አባላትም በሁለቱ ዳይሬክተሮች አቶ አወል ሱልጣን እና አቶ ኖህ ታከለ ከቀረላቸው ማብራሪዎች በመነሳት ድጋፍ ስለሚያደርጉባቸው የትኩረት መስኮች ተገቢውን መረጃ መያዝ መቻላቸውን ገልጸው የተቋሙን ተጨባጭ ሁኔታ ከሌሎች ሀገራት ልምዶች ጋር በማጣጣም የተቋሙን የተግባቦት ስራ ደረጃ ከፍታ ለመጨመር የሚያስችሉ ድጋፎችን እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡