የፍትሕ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች በሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የመንግስት ሰራተኞች የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ የሚቀርቡ አጀንዳዎችን የማሰባሰብ እና የመለየት ውይይት አካሔዱ

Ministry of Justice and Affiliated Institutions Staff Conducted Discussion to Collect and Identify Agendas for the National Dialogue Commission's Public Servants Agenda Collection Forum

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች ለሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የመንግሥት ሰራተኞች የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ የሚቀርቡ አጀንዳዎችን የማሰባሰብ እና የመለየት ውይይት ግንቦት 12/2017 ዓ.ም አካሂደዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር 1265/2014 ከተቋቋመ በኋላ በመላ ሀገሪቱ አጀንዳ የማሰባሰብ እና የመለየት ስራ እያከናወነ ይገኛል። በዚህም መሠረት ኮሚሽኑ አጀንዳ ከሚያሰባስብባቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች መካከል የመንግሥት ሰራተኞች የሚገኙበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በፌደራል የመንግሥት ተቋማት የአጀንዳ ማሰባሰብ እና ልየታ ስራ ተጀምሯል፡፡ በዚህም መነሻነት የፍትሕ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች በዛሬው መድረክ የአጀንዳ ማሰባሰብና ልየታ አካሂደዋል፡፡ የውይይት መድረኩን የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ በላይሁን ይርጋ በንግግር ከፍተዋል።

የሠራተኛ የውይይት መድረኩን የሚመሩ እና አጀንዳ የማሰባሰብ ስራውን የሚያስተባብሩ ሰብሳቢ እና ፀሀፊ በተሳታፊዎች በመምረጥ ሰፋ ያለ ውይይት በማካሄድ አጀንዳ የማሰባሰብና የመለየት ስራው ተከናውኗል። ከዚህ በተጨማሪም በዚሁ መድረክ የፍትሕ ሚኒስቴርን እና ተጠሪ ተቋማትን በቀጣይ በሚካሄደው የኮሚሽኑ አጠቃላይ የፌዴራል ተቋማት የመንግሥት ሰራተኞች የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ላይ የሚወክሉ ሠራተኛ ተመርጠዋል።

Tagged Under: Affiliated Institutions • african charter on the rights and welfare of the child • african commission on human and peoples' rights • age • and healthcare administration and control authority • arra (agency for refugees and returnees affairs) • collection • commission • conduct • dialogue • Discussion • Forum • institution • institutions • itu • Justice • ministry • ministry of public service and human resource development • mission • National • National Dialogue • national dialogue commission • national discussion forum • public • public servants • servants • staff
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች