በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳሬክቶሬት ተዘጋጅቶ በተለያየ ዙር የተቋሙን ዐቃብያነሕግ አቅም ለማሳደደግ ታሳቢ ያደረገና በስራ ላይ የሚያጋጠሙ ጉዳዮች በይበልጥ በተግባር ተደግፈው የሚቀርቡበት የክረምት ሥልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡
በሙስና ወንጀሎች ምርመራና ክስ ዝግጅት ላይ ትኩረት አድርጎ ከጳጉሜ 03-05 2017 ዓ.ም የሚሰጠው ይህ ሥልጠና በዋነኝነት በሙስና ወንጀሎች ሕግ አተገባበር፣ በወንጀል የተገኘ ንብረትን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ፣ በሙስና ወንጀል እና money laundry ምርመራ እና ክስ አቀራረብ ተግባር ላይ ትኩረት ያደረጉ ጉዳዮች ዙሪያ የሚሰጥ ሥልጠና መሆኑ ተገልፃል።
በፍትሕ ሚኒስቴር ስር ከሚገኙት ድሬደዋ፣ ሀዋሳ እና አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችና የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳሬክቶሬት የተወከሉ በሙስና ወንጀሎች ላይ የሚሰሩ ዐቃብያነ ሕግ የሚሳተፉበት ሲሆን፤ ሥልጠናው ባለሙያዎቹ እውቀትና ክህሎት እንዲያገኙ የማድረግ፣ ዐቃብያነ ሕግ እርስ በርስ ልምድና ተሞክሮቸውን በመለዋወጥ እንዲማማሩ የማድረግ እንዲሁም ያላቸውን እውቀት እንዲያስታውሱ የማድረግ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ተጠቅሷል፡፡ በተጨማሪም መድረኩ በተግባር ላይ ያተኮሩ ጉዳዮች እየተነሱ ሥልጠና የሚሰጥበት መሆኑ በቀጣይነት በስራ ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በቀላሉ እየፈቱ ለመሄድ የሚያስችል እውቀትና ክህሎት የሚፈጠርበት እንዲሁም ከሙስና ወንጀሎች ጋር ተያይዞ የሚከናወኑ የቅድመ ምርመራ ተግባራት እና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የባለሙያዎቹን አቅም የመገንባት ጠቀሜታ እንዳለው ተጠቅሷል፡፡
በተቋሙ ማኔጅመንት ተፈቅዶ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ለዐቃብያ ሕግ እየተሰጠ የሚገኘው የክረምት ስልጠና በተለይም በወንጀል ምርመራ፣ በክስ ዝግጅትና ችሎት ክርክር፣ በኢኮኖሚ ወንጀሎች ክስ ዝግጅትና ችሎት ክርክር በተለያዩ ዙሮች በድሬደዋ እና አዲስ አበባ ሥልጠና ተዘጋጅቶ እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡ በዚህ ከጳጉሜ 03-05 2017 ዓ.ም በሚካሄደው ሥልጠና አጠቃላይ በሙስና ወንጀሎች ዙሪያ የባለሙያዎችን አቅም ከመገንባት ባለፈ፡ አከራካሪ በሆኑ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዙሪያ ዐቃብያነ ሕግ ተቀራራቢ የሆነ አቋም እንዲኖራቸው በማድረግ በቀጣይነት ተመሳሳይ የሆነ ስራ ማከናወን የሚያስችል እውቀትና ክህሎት የሚፈጠርበት መሆኑ ተመልክቷል፡፡