በፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ህግ ትምህርትና ሥልጠና ዳሬክቶሬት የተዘጋጀና ትኩረቱን የሠራተኞች ሙያዊ እና የስራ ላይ ስነ-ምግባር እንዲሁም የዓሠራር ሥርዓቶች ላይ ያደረገ ሥልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡
የፍትሕ ሚኒስቴር በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሥልጠና በማዘጋጀት አጠቃላይ ያለውን የሠው ኃይል የመገንባት ተግባር በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም መሠረት ያለውን የሥልጠና ፍላጎት የዳሰሳ ጥናት በማድረግ ባለፉት 6 ወራት ፍላጎትን መሠረት ያደረጉ ከ500 በላይ ዐቃብያነ ሕግ እንዲሁም ለ200 አመራሮች እና ከ250 በላይ የአስተዳደር ሠራተኞች በሥራ ላይ ያተኮሩ ሥልጠናዎችን በመስጠት ያለውን የሠው ኃይል አቅም የመገንባት ሥራ መከናወኑ ተመላክቷል፡፡
ሠራተኞችን በሥራ እና ሞያዊ ስነ-ምግባሮች ላይ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ በተለያየ ጊዜ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በማዘጋጀት ሠራተኛው የሙያና ስነ-ምግባር ሁኔታውን እንዲመለከት ማድረግ የተሻለ አገልግሎትን ለመስጠት በሚችልበት ብቃት ላይ እንዲገኝ የሚያደርገው መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ለሁለት ቀናት የሚሰጠው ዚህ ሥልጠና ዋነኛ አላማም የሠራተኞች በሥራ እና የሙያ ስነ-ምግባር ላይ ያላቸውን እውቀት እንዲያሳዳጉ በማድረግ በሥራ ላይ ደንበኞችን ማርካት የሚያስችል አገልግሎት እንዲሰጡ ማዘጋጀት መሆኑ ተገልጻል፡፡
በስነ-ምግባር ምንነት፤ ባሕሪያት፤ እሴቶችና ጠቀሜታ እንዲሁም በመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ መሠረት በዲሲፕሊን የሚያስጠይቁ ጉዳዮች ተነስተው ውይይት በሚደረግበት በዚህ የስልጠና መድረክ ለይ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከተለያዩ ዳሬክቶሬቶች፣ ከድሬደዋ፣ ሀዋሳ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከሚገኙ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የተወከሉ የአስተዳደር ሠራተኞች የተሳተፉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ሠራተኛ በግል የሚያበረክተው አስተዋጽኦ በጋራ ፍትሕ ሚኒስቴር ተገልጋይ ተኮር የሆነ አገልግሎትን መስጠት እንዲችል የሚያደርግ መሆኑን ተገንዝቦ ምንጊዜም ቢሆን ሠራተኛው ሥራው የሚጠየቀውን ሙያ እና ስነ-ምግባር አሟልቶ መገኘት የሚጠበቅበት መሆኑ ተገልፁዋል፡፡