በሕግ ጥናት ስነ-ዘዴዎች ላይ ያተኮረ የዐቅም ግንባታ ሥልጠና መሰጠቱ ተመላከተ

A capacity building training focused on legal study methodologies was given.

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ ትኩረቱን በሕግ ጥናት ስነ-ዘዴዎች ላይ ያደረገ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ለዐቃብያነ ሕግ በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡

ከመስከረም 08-09 ቀን 2018 ዓ.ም በሚሰጠው በዚህ ሥልጠና ላይ ከፍትሕ ሚኒስቴር የሕግ ማርቀቅ፣ ከፌዴራል ሕጎች ተፈፃሚነት እንዲሁም ከንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬቶች፣ ከጠበቆች ቦርድ፣ ከወንጀል ሥነ ሥርዓት ጽ/ቤት እንዲሁም ከሙስና እና ስነ ምግባር መከታተያ እና ከሌሎችም ለተወከሉ ዐቃብያነ ሕግ የተዘጋጀውን ሥልጠናው የሰጡት ከ Institute for security studies የመጡ የሕግ ተመራማሪ ሲሆኑ፤ ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ሥልጠና ለተቋሙ በሕግ የተሰጡትን ስልጣንና ኃላፊነቶች ለመወጣት እንዲቻል የሚደረጉ ጥናቶች ትክክለኛ እና ሳይንሳዊ ዘዴዎች ላይ ብቻ ተመስርተው የሚሰሩ እንዲሆኑ ማድረግ የሚረዱ ርዕሰ ጉዳዮች በስፋት ተነስተው ውይይት የሚደረግባቸው መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

የፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳሬክቶሬት ባደረገው የሥልጠና ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት መሠረት Legal research and methodology ላይ የአቅም ግንባታ ሥልጠና በማኔጅመንት አስፈላጊነቱ ታምኖበት እንዲዘጋጅ የተደረገው ይህ የሥልጠና በቀጣይነት በተቋሙ ውስጥ የሚሰሩ የሕግ ጥናቶች ትክክለኛውን ሳይንሳዊ ስነ-ዘዴ ተከትለው መሰራት እንዲችሉ በማድረግ በዚህም ችግር ፈቺ የሆኑ የሕግ ጥናቶችን መስራት የሚያስችል አቅምን የመፍጠር አላማ ያለው የሥልጠና መድረክ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ዐቃብያነ ሕግ በሥራቸው ላይ ያላቸውን እውቀት በየደረጃው ማሳደግ እንዲችሉ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን አዘጋጅቶ መስጠት ለተቋሙ የተሰጠ ተግባር በመሆኑ በሕግ ጉዳዮች ላይ ጥናት ለሚሰሩ ባለሙያዎች ከሥራቸው ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያለውና ወቅቱን የጠበቀ ሥልጠና መሰጠቱ በቀጣይነት የሚደረጉ ጥናቶችን ሳይንሳዊ ስነ-ዘዴን ተከትለው እንዲከወኑ ማድረግ ያስችላል፡፡ በሌላም በኩል ክፍተት አለባቸው ተብለው በተለዩ ጉዳዮች እንዲሁም ከሌሎች የሥራ ክፍሎች በሚቀርቡ ጥያቄዎች መሠረት የሚደረጉ የጥናት ሥራዎችን የበለጠ ውጤታማ አድርጎ ማከናወን የሚያስችል አቅም የሚፈጠርበት መሆኑ የተገለጠ ሲሆን፡ በሕግ ጥናት ስነ-ዘዴዎች ላይ ያተኮረው ይህ የዐቅም ግንባታ ሥልጠና ተቋሙ 5ኛው የክረምት ልዩ መረሀ ግብር ሥልጠና መሆኑ ተመላክቷል፡፡

Tagged Under: academic building capacity Capacity Building capacity building training city court ecu Education institute itu judicial judiciary learning legal legal research methodology res Research school sea search Security studies study Training Use used
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች