የሴቶችን የፍትህ፣የምክክር እና ስርአተ ጾታ እኩልነትን ለማረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በመተባበር ተከታታይነት ያለዉና ዉጤትን መሰረት ያደረገ ስራ ሊሰሩ እንደሚገባ ተመላከተ ● Call for Coordinated and Results-Oriented Action to Advance Women's Access to Justice, Dialogue, and Gender Equality

Call for Coordinated and Results-Oriented Action to Advance Women's Access to Justice, Dialogue, and Gender Equality

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ከጀስቲስ ፎር ኦል (ፍትሕ ለሁሉም) እና ከፈረንሳይ ኤምባሲ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ባለፉት ሁለት አመታት የዘለቀ የፍትሕ የምክክርና የስርአተ ጾታ እኩልነት ፕሮጀክት ማጠቃለያ መርሃ ግብር ሐምሌ 16 ቀን 2ዐ17 ዓ.ም ከተለያዩ ተቀማት የተዉጣጡ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በአዲስ አበባ ተካሂደል፡፡

በመርሃግብሩ ላይ ተገኝተዉ መልእክት ያስተላለፉት የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ኤርሚያስ የማነብርሃን (ዶ/ር) ፍትሕ ሚኒስቴር ስርአተ ጾታን እዉን በማድረግ በኩል በሕግ የተሰጡትን ኃላፊነቶች መሠረት አድርጎ በራስ አቅም እና ከአጋር አካላት ጋር በርካታ ስራዎችን ሲያከናዉን መቆየቱን ገልፀዋል፡፡

ከነዚህ ግባራት ዉስጥ አንዱ የሆነዉና ላለፉት ሁለት አመታት ቆይታ የነበረዉ የፍትሕ የምክክርና ስርአተ ጾታ ፕሮግራም (justice dialogue and gender equality program) አንደኛዉ መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትር ዲኤታዉ የስርአተ ጾታ ፍትሕን በማረጋገጥ ጾታዊ ጥቃትን አስመልክቶ በሚሰሩ ስራዎች አጋርነትን ማጠናከርና በኢትዮጵያ የብሔራዊ ምክክር ሂደት ተሳታፊ እንዲሆኑ ማስቻል የሚሉ ዋነኛ ዓላማዎች ላይ ተመስርቶ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን አንስተዋል፡፡

አያይዘዉም ከስርአተ ጾታ ጋር ተያይዞ ከተሰሩ ስራዎች መካከልም የፍትሕ እንክብካቤ ማዕከላት ከተቋቋሙበት ዓላማ አንፃርና እያደገ ከመጣዉ የተገልጋዮች ፍላጎት ጋር ያሉ ክፍተቶችን የመለየት ስራ መከናወኑንና በተጨማሪም ተጎጂዎች ያለባቸዉን አቤቱታ ሥርዓት ባለዉ መንገድ እንዲያቀርቡ ለማድረግ የሚያስችል ማንዋል መዘጋጀቱን ለአብነት አንስተዋል።

በተጨማሪም የጾታዊ ጥቃት ፍትሕን የማስፈን ኃላፊነትን ለመወጣት ጥረቶች እየተደረጉ እንደሆነ አክለዉ ለዚህ ተግባር እዉን መሆንም ስትራቴጅ ተዘጋጅቶ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ስራዎችን ለመሥራት ጥረት እየተደረገ እንዳለ ገልጸወ ይህ ተግባር ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በቀጣይም በሁለት አመቱ ፕሮጀክት የተሰሩ ስራዎችንና ጥረቶችን በማጠናከር መሬት ላይ ያለዉን ተጨባጭ ሁኔታ ተረድቶ ዉጤት ላይ በማተኮር ተቋማት በጋራ አብረዉ ሊሰሩ እንደሚገባ አመላክተዉ ለፕሮጀክቱ መሳካት ድጋፍ ያደረጉ የፈረንሳይ ኤምባሲ፣ፍትሕ ለሁሉም(ጀስቲስ ፎር ኦል) እንዲሁም ስራዉን በጋራ ሲያከናዉኑ ለቆዩት ባለድርሻ ተቋማት ምስጋና አቅርበዋል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የፈረንሳይ ኤምባሲ፣የፍትሕ ለሁሉም(ጀስትስ ፎር ኦል)፣የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ፣የሰላም ሚኒስቴር ተወካዮች መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን የቀድሞ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ አጠቃላይ ፕሮጀክቱን የሚመለከት ገለፃና የአገራት ልምድ አቅርበዋል፡፡

ቀጥሎም ፕሮጀክቱ ስራ ከጀመረበት ካለፈዉ ጁን 2023 ጀምሮ እስካሁን ባለዉ ሂደት የተከናወኑ ተግባራት በፕሮጀክቱ ባለድርሻ አካላት አማካኝነት የቀረበ ሲሆን ፕሮጀክቱ በዋናነት ሴቶችን በሰላምና ፀጥታ ብሎም በሌሎች ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ እንዲጨብጡ በማድረግ በኢትዮጵያ ምክክር መድረክ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ በማስቻል የሴቶችን ተሳትፎ ማረጋገጥ ዋነኛ ዓላማዉ ሲሆን በዚህም ከአቅም ግንባታ ስራዎች ጋር በተያያዘ ሥልጠናዎችን በመስጠት ፣ጥናቶችን በማድረግ፣የሕግ ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ሕግ ማርቀቅ፣ የወሲባዊ ጥቃት ወንጀሎችን በተፋጠነ እና ተጎጅ ተኮር በሆነ መንገድ መዳኘት የሚያስችል ማንዋል ማዘጋጀትና ሌሎቸ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ማከናወን መቻሉ በመድረኩ ተገልጿል።

የቅርብ ጊዜ ዜናዎች