ከመስከረም 08-09 ቀን 2018 ዓ.ም በሚሰጠው በዚህ ሥልጠና ላይ ከፍትሕ ሚኒስቴር የሕግ ማርቀቅ፣ ከፌዴራል ሕጎች ተፈፃሚነት እንዲሁም ከንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬቶች፣ ከጠበቆች ቦርድ፣ ከወንጀል ሥነ ሥርዓት ጽ/ቤት እንዲሁም ከሙስና እና ስነ ምግባር መከታተያ እና ከሌሎችም ለተወከሉ ዐቃብያነ ሕግ የተዘጋጀውን ሥልጠናው የሰጡት ከ Institute for security studies የመጡ የሕግ ተመራማሪ ሲሆኑ፤ ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ሥልጠና ለተቋሙ በሕግ የተሰጡትን ስልጣንና ኃላፊነቶች ለመወጣት እንዲቻል የሚደረጉ ጥናቶች ትክክለኛ እና ሳይንሳዊ ዘዴዎች ላይ ብቻ ተመስርተው የሚሰሩ እንዲሆኑ ማድረግ የሚረዱ ርዕሰ ጉዳዮች በስፋት ተነስተው ውይይት የሚደረግባቸው መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
የፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳሬክቶሬት ባደረገው የሥልጠና ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት መሠረት Legal research and methodology ላይ የአቅም ግንባታ ሥልጠና በማኔጅመንት አስፈላጊነቱ ታምኖበት እንዲዘጋጅ የተደረገው ይህ የሥልጠና በቀጣይነት በተቋሙ ውስጥ የሚሰሩ የሕግ ጥናቶች ትክክለኛውን ሳይንሳዊ ስነ-ዘዴ ተከትለው መሰራት እንዲችሉ በማድረግ በዚህም ችግር ፈቺ የሆኑ የሕግ ጥናቶችን መስራት የሚያስችል አቅምን የመፍጠር አላማ ያለው የሥልጠና መድረክ መሆኑ ተመልክቷል፡፡