የጠበቆች አስተዳደር ቦርድ ከፌደራል የጠበቆች ማህበር አመራሮች እና ለቦርዱ ተጠሪ ከሆኑ አደረጃጀቶች ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ

Lawyers' Administration Board Holds Consultation Forum with Federal Bar Association Leaders and Subordinate Organizations

በምክክር መድረኩ የጠበቆች አስተዳደር ቦርድ አባላት፣ የፌደራል የጠበቆች ማኀበር አመራሮች፣ የጠበቆች ዲስፕሊን ጉባኤ አባላት፣ የጥብቅና ሙያ መግቢያ ፈተና ኮሚቴ አባላት እና የጥብቅና ፍቃድ ገምጋሚ ኮሚቴ አባላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የጠበቆች አስተዳደር ቦርድ ፀሐፊ አቶ ወንድሙ ግዛው ባስተላለፉት መልዕክት የጥብቅና አገልግሎት ፈቃድ አሰጣጥና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2013 የጥብቅናን ሙያ አገልግሎት በላቀ ሥነ-ምግባርና ብቃት እንዲመራ እና ጠበቆች ሙያቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ በማድረግ ረገድ ፈር ቀዳጅ ሕግ በመሆኑ ይህንኑ እውን እንዲሆን በተለይም የፌደራል ጠበቆች ማህበርን ማጠናከርና ራሱን ችሎ እንዲንቀሳቀስ ለማስቻል ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበት ገልጸው የጠበቆች አስተዳደር ቦርድ እና ተጠሪ አደረጃጀቶች አባላት እንዲሁም የማህበሩ አመራሮች የተጣለባቸውን ከባድ ኃላፊነት በትጋት እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

በመቀጠልም ውይይቱን የመሩት የጠበቆች ቦርድ አባል የሆኑት አቶ ታምሩ ወንድማገኘሁ እና የጠበቆች አስተዳደር ቦርድ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ሊያ ተክሌ የመድረኩ ዋና ዓላማ በአዋጁ መሠረት የተቋቋሙ አደረጃጀቶች አመራሮችና አባላት የትውውቅ እና እነዚሁ አካላት ሲያከናውኗቸው የነበሩ ሥራዎችን ከግምት በማስገባት በቀጣይ በትኩረት ሊሰሩ የሚገቡ ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ የጋራ መረዳትን ለመፍጠር መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በመድረኩ የተገኙ ተሳታፊዎችም በቀጣይ በሚሰሩ ዋና ዋና ስራዎች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡

በመጨረሻም በአዋጁ መሠረት ሊወጡ የሚገቡ የሕግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት ወደ ሥራ እንዲገቡ ማድረግ፣ የጥብቅና ሙያውን ለማጎልበት የሚረዱ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ወደ ሥራ ማስገባት፣ የጠበቆች የሙያ ሥነ ምግባር ላይ ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ ማድረግን ትኩረት ሰጥቶ ለመሥራት በመስማማት መድረኩ ተጠናቋል፡፡

Relevant Departments and People
Tagged Under: administration Advocacy association bar board committee conduct continuing legal education disciplinary disciplinary committee ethics federal federal bar association framework Lawyers Lawyers' Administration Board legal Legal ethics legal framework Legal Profession Legal Reform Legal Services Licensing licensing committee profession professional professional conduct professional development regulatory compliance
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች