ለታራሚዎች በተደራጀ መልኩ የንቃተ ሕግ ግንዛቤ ለመፍጠር የሚያስችል የማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ተካሄደ

Initiative Launched to Strengthen Legal Awareness for Prison Inmates

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ ትምህርት እና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት በቀጣይ በአዲስ አበባ እና በክልል ማረሚያ ቤቶች ለሚገኙ ታራሚዎች በተደራጀ መልኩ የንቃተ ሕግ ግንዛቤ መፍጠሪያ ሥልጠና ለመስጠት የሚያስችለውን የማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም አካሂዱዋል፡፡

እንደሚታወቀው በአዋጅ ቁጥር 943/2008 እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር 1263/2014 ለፍትሕ ሚኒስቴር ከተሰጡት ኃላፊነቶች መካከል ለተጠሪ ተቋማት የንቃተ ሕግ ትምህርት እና ሥልጠና በመስጠት የአቅም ግንባታ ማድረግ እንዲሁም ተቋማቱን መደገፍ እና ማጠናከር ኃላፊነት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

በዚህም መሰረት በዛሬዉ ዕለት የፍትሕ ሚኒስቴር እና የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በጋራ በመሆን በቀጣይ በአዲስ አበባ እና በክልል ማረሚያ ቤቶች ለሚገኙ ታራሚዎች በተለያዩ የሕግ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ባለሙያዎችን በመጋበዝ ሥልጠና ለመስጠት የሚያስችላቸዉን የማስጀመሪያ መርሃ-ግብር አካሂደዋል፡፡

የንቃተ ሕግ ሥልጠናዉ ታራሚዎቹ በማረሚያ ቤት ቆይታቸዉ እንዲሁም ከወጡ በኋላ ከማኅበረሰቡ ጋር ሲቀላቀሉ ሕግን አክብረዉ ለመኖር እንደሚያግዛቸዉ የተገለፀ ሲሆን፣ በማረምና ማነፅ ሂደት ውስጥ የሚሳተፉ በየደረጃው ያሉ የሚመለከታቸው አካላት እንዲሁ ሕግ እና ሥርዓትን ተከትለው ኃላፊነታቸዉን እንዲወጡ ስለሚያስችል በቀጣይ በተካታታይ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራዉ እንደሚቀጥል ተገልፆል፡፡

በመጨረሻም በፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ ትምህርት እና ሥልጠና አማካኝነት የተዘጋ ጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፅሑፍ ለኮሚሽኑ ተበርክቷል፡፡

Tagged Under: 1263/2014 943/2008 act african charter on the rights and welfare of the child Awareness Convention on the Rights of the Child court decree initiative judge judicial judiciary launch law legal Legal Awareness legislation Policy prison proclamation Regulation statute tribunal un war
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች