የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ለኮማንደር ደራርቱ ቱሉ የረዳት ኮሚሽነርነት ማዕረግ ሰጠ

Federal Prison Commission Hosts Support Commissioner General's Forum

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ዘሬ በሸራተን አዲስ ባካሄደው የዕውቅና መርሃ ግብር በሕግ ማስከበር ዘመቻው ለበረከቱና እና በስራ አፈፃፀም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የተቋሙ አመራሮችና አባላት እውቅናና የማዕረግ እድገት ሰጥቷል፡፡

በመረሃ ግብሩም ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮ/ር ደራርቱ ቱሉና በርካታ ጀግኖች አትሌቶችን ላፈሩት አንጋፋው አሰልጣኝ ኮ/ር ሁሴን ሼቦ የረዳት ኮሚሽነርነት ማዕረግ ሰጥቷል፡፡

በመርሃግብሩ ላይ የኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ተገኝተው የረዳት ኮሚሽነርነት ማዕረጉን በማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ዳመና ዳሮታ አቅራቢነት ሰጥተዋል፡፡በመድረኩ በኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ሰብሳቢ ወ/ሮ እጸገነት መንግሥቱ፣ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ፣ የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል::

Tagged Under: achievement • armed forces • army • athletics • award ceremony • commission • ethiopian federal police • federal • federal prison commission • gideon timotheos • house of peoples’ representatives • Law Enforcement • Military • Police • prison • recognition • Security • soldiers • sports • supreme court
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች