በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር በጠቅላይ ዐ/ሕግ ዘርፍ የአዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከክፍለ ከተማው ፍትሕ አካላት ጋር በመሆን ለመርማሪ ፖሊሶች ስልጠና ሰጠ

FDRE Ministry of Justice Attorney General Sector Addis Ketema Branch Office Provided Training to Investigative Police in Collaboration with Sub-City Justice Bodies

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የአዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከወንጀል ምርመራ ጋር በተያያዘ ከክፍለ ከተማው ፍትሕ አካላት ጋር በመሆን በክፍለ ከተማው ለሚገኙ መርማሪ ፖሊሶች እና ዐቃቤያነ ሕጎች ለሁለት ቀን ሥልጠና ሰጥቷል።

የአዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ተሻለ ዮሴፍ በሥልጠናው ወቅት እንደገለፁት ሥልጠናው ከወንጀል ምርመራ ጋር በተገናኘ መርማሪዎች ስራቸውን ሲሰሩ አቤቱታ ከመቀበል፣ ማስረጃዎችን ከማሰባሰብ፣ ተጠርጣሪን ቃል ከመቀበል እና ሰበአዊ መብቶችን ከመጠበቅ አንጻር፣ ከጊዜ ቀጠሮ መጠየቅ እና ከብርበራ እንዲሁም ከኢጊዚቢት አያያዝ ብሎም ተያያዥ ማስረጃ አሰባሰብ ጋር በተገናኘ የወንጀል ምርመራ ላይ ያተኮረ መሆኑነን ገልፀዋል።

በሥልጠና መድረኩ ከምርመራ ስራዎች ጋር በተገናኘ በክፍለ ከተማው የነበሩ ችግሮችን በስፋት በማንሳት እና የታዩ ችግሮችን በመፍታት ምርመራን እንዴት በሚፈለገው መንገድ ማስቀጠል ይቻላል በሚሉ ጉዳዩች ላይ ስፋ ያለ ውይይት ተደርጓል።

የሥልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ሥልጠናው አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው፤ የወንጀል ምርመራ ስራን በአግባቡና በሚፈለገው ጥራት ማከናወን የተጠናከረ የፍትሕ ተቋም ባለቤት ለመሆን፣ ለአገሪቱ ዲሞክራሲ ስርዓት መጎልበት፣ ለኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለህብረተሰቡ ሰላም እና ደኅንነት መረጋገጥ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ተናግረዋል።

በመጨረሻም ሥልጠናው በሚፈለገው ልክ እንዲከናወን ድጋፍ ላደረጉ እና ለተባበሩት ለከፍል ከተማው የፍትሕ አካላት ምስጋና በማቅረብ ተጠናቋል፡፡

Tagged Under: addis attorney Attorney General civil liberties criminal Criminal Investigation democratic democratic governance Due Process Economic development evidence collection FDRE federal federal democratic republic of ethiopia (fdre) forensic science fundamental rights general Human Rights ketema Legal Training Police Police Training republic Rule of Law
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች