ከፍትሕ ተደራሽነት እና የህግ ድጋፍ ጋር በተያያዘ በሀገራችን እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ለተለያዩ ሀገራት እና ለአለማቀፍ ተቋማት ተወካዮች ቀረቡ

Ethiopia Presents Works on Access to Justice and Legal Aid to Representatives of Various Countries and International Organizations

ከፍትሕ ሚኒስቴር እና ከፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የተከላካይ ጠበቆች ጽ/ቤት የተውጣጣ ልኡክ በኦስትሪያ ቬይና እ.ኤ.አ. ከሜይ 19-23 ቀን 2025 ዓ.ም ድረስ እየተካሔደ ባለው የተባበሩት መንግሥታት 34ኛው የወንጀል መከላከልና የወንጀል ፍትሕ ኮሚሽን (Commission on Crime Prevention and Criminal Justice) ኮንፈረንስ ላይ ከፍትሕ ተደራሽነት እና የሕግ ድጋፍ (Access to Justice and Free Legal Aid) ጋር በተያያዘ በሀገራችን እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለተለያዩ ሀገራት እና ለአለማቀፍ ተቋማት ተወካዮች አቀረበ፡፡

በኮንፈረንሱ ሀገራችን በመወከል ንግግር ያደረጉት በፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በረከት ማሞ በአሁኑ ጊዜ እየመጡ ያሉ አዳዲስ ወንጀሎችን ጨምሮ የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን አስመልክቶ በሀገራችን እየተከናወኑ ስላሉ ተግባራት ገለጻ አድርገዋል፡፡

ከኮንፈረንሱ ጎን ለጎን ልዑኩ ‘’የፍትሕ ተደራሽነት እና የሕግ ድጋፍ በኢትዮጵያ (Access to Justice and Free Legal Aid)’’ በሚል ባዘጋጀው የጎንዮሽ መድረክ በሀገራችን ስላለው የፍትሕ ተደራሽነት፣ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ስላለበት ሁኔታ እንዲሁም በቀጣይ ከሕግ ድጋፍ አገልግሎት ጋር በተያያዘ እየተሰሩ ስላሉ ስራዎች በመድረኩ ለታደሙ የተለያዩ ሀገራት እና አለማቀፍ ተቋማት ተወካዮች በማቅረብ የልምድ ልውውጥ አድርጓል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ልዑኩ በሀገራችን ከሕግ ድጋፍ አገልግሎት ስራዎች ጋር በተያያዘ እየተከናወኑ ስላሉ ስራዎችና በቀጣይ የታቀዱ ትላልቅ ተግባራትና የሚያስፈልጉ ድጋፎች ዙሪያ መቀመጫውን አሜሪካ ካደረገ International Legal Foundation ከተባለ አለማቀፍ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ Mrs. Jennifer Smith ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርጓል፡፡

ልዑኩ በዚህ ኮንፈረንስ እንዲሳተፍ የተባበሩት መንግስታት አደገኛ ዕጾችና ወንጀሎች መቆጣጠሪያ ቢሮ (UNODC) ድጋፍ አድርጓል፡፡

Tagged Under: access Access to Justice aid Bilateral Discussions commission Crime criminal Criminal Justice ethiopia's justice sector federal federal supreme court foundation international international organizations Justice Justice System Reform legal Legal Aid legal aid services Organized Crime prevention Transnational crime UNODC vienna
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች