ኢትዮጵያና ስዊዘርላንድ በፍልሰት ጉዳዮች ላይ ትብብራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለፀ

Ethiopia and Switzerland Held Bilateral Discussion to Strengthen Migration Cooperation Geneva, Switzerland

በስዊዘርላንድ ጄኔቫ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (International Organization on Migration) 116ኛው ምክር ቤት የሚኒስትሮች ስብሰባ የተሳተፉት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኤርምያስ የማነብርሃን ከስዊዘርላንድ የፍልሰት ጉዳዮች ስቴት ሴክሬታሪ ክቡር ሚስተር ቪንሴንዞ ማሲዮሊ ጋር በፍልሰት ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡

ከድርጅቱ ምክር ቤት ስብሰባ ጎን ለጎን በተካሄደው በዚሁ የሁለትሽዮች ውይይት ወቅት ክቡር ሚኒስትር ዴዔታው የኢትዮጵያን የፍልሰት ነባራዊ ሁኔታዎች፤ ፈታኝ ተግዳሮቶች እንዲሁም ምቹ ሁኔታዎችን በተመለከተ ለስዊዘርላድ አቻቸው አብራርተዋል፡፡

ሚኒስትር ዴዔታው አያይዘውም ሁለቱ አገራት በፍልሰት ዙሪያ በጋራ እየሰሩባቸው የሚገኙ ጉዳዮችን በመግለጽ ኢትዮጵያ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከል፤ተጎጂዎችን መልሶ በማቋቋም እንዲሁም መደበኛ ፍልሰትን ለማጠናከር ለምታደርገው ጥረት የስዊዘርላንድ መንግስት እያደረገ ያለውን ሰፊ ድጋፍ አንሰተው ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በመጨረሻም ሁለቱ አገራት በፍልሰት ጉዳዩች ላይ ትብብራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሎ በመግለፅ በቀጣይ ትኩረት አድርገው በሚሰሩባቸው ጉዳዩች ላይ መክረዋል፡፡

Tagged Under: african charter on the rights and welfare of the child and healthcare administration and control authority bilateral Bilateral Cooperation constitution of the federal democratic republic of ethiopia Convention on the Rights of the Child convention on the rights of the child (crc) Cooperation Discussion ethiopia revenue and customs authority geneva Inter agency cooperation international international civil aviation organization (icao) international convention on civil and political rights International Cooperation international covenant on civil and political rights international organization for migration international organization for migration (iom) iom (international organization for migration) land Migration National national migration cooperation coordination office operation organ organization per ratio switzerland
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች