በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ ተስፋዬ ዳባ ከደቡብ ኮሪያ ሪፐብሊክ የኢትዮጵያ አምባሳደር ከሆኑት ክቡር Mr. JUNG KANG ጋር በሕግ ጉዳይ በትብብር በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
በዉይይታቸዉም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታዉ እንደገለፁት የኢፌዴሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ዋና ኃላፊነት በአገሪቱ የሚፈፀሙ የተለያዩ ወንጀሎች ምርመራና ክርክር በማድረግ ወንጀለኞችን ተጠያቂ ማድረግ መሆኑን ገልጸው ኢትዮጵያና ኮሪያ ካላቸው ታሪካዊ ግንኙነት ረገድ ከንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት በተጨማሪ በሕግ ጉዳዮች ትብብር፣ መረጃና ልምድ ልውውጥ በማድረግ ተቋማት በማጠናከር በጋራ መሥራት እንሚገባቸው አንስተዋል፡፡
ክቡር Mr. JUNG KANG በበኩላቸው ኢትዮጵያ እና ደቡብ ኮሪያ በንግድና ኢንቨስትመንት ረገድ መልካም ግንኙት ያላቸው መሆኑን ጠቅሰው በሀገሪቱ ያሉ ኢንቨስተሮች ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠርላቸውና ተገቢውን የሕግ ጥበቃ እንዲያገኙ ማድረግ እንዲገባ ገልጸው ሀገራቸው በሕግ ጉዳይ ከፍትሕ ሚኒስቴር ጋር አብረው ለመሥራት ፍላጎት ያላቸው መሆኑን በውይይቱ ወቅት ጠቅሰዋል፡፡