ለፍትሕ ሚኒስቴር ተጠሪ ከሆኑ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን የ2014 በጀት ዓመት የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸሙን ከባለድርሻ አካላት ጋር እየገመገመ ይገኛል፡፡
በመድረኩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የፍትሕ ሚንስቴር ሚኒስትር ደኤታ አለምአንተ አግደው እንደገለጹት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በሃገራችን የልማት እንቅስቃሴ እና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የማይተካ ሚና እንዳላቸው በመንግሥት በኩል ጽኑ እምነት አለ ያሉ ሲሆን የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በታሪክ የተፈጠረላቸውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በሃገራዊ ጉዳዬች ላይ በተለይም የሕግ የበላይነት በማረጋገጥ፣ሰላምን በማስፈንና ግጭቶችን በመፍታት ሂደት ትርጉም ባለው መልኩ አዎንታዊ ሚና መጫወት ይኖርባቸዋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ከግዜ ወደ ግዜ የተሻለ አቅም እየገነቡ እና መልካም አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆኑን በሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡ በሃገራዊ ጉዳይ ሲማዶች በጦርነትና በድርቅ ለተጎዱ አከባቢዎችና የህብረተሰብ ክፍሎች በገንዘብና በዓይነት እያደረጉ ያሉት ድጋፍ አንድ ለሕዝብ ተጠቃሚነት ከቆመ ዘርፍ የሚጠበቅ በመሆኑ ምስጋና የሚገባው መሆኑን በመጠቆም ሲማዶች በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይም ሆነ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ እያደረጓቸው ያሉት አስተዋጽኦዎች መንግሥት ከፈጠረው ምቹ ሁኔታ እና ከአገርና ሕዝብ ፍላጎት አንጻር አሁንም ብዙ የሚቀረው ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ዘርፉ ሕግና ስርዓትን ተከትሎ ውጤታማ ስራ እንዲያከናውን የጀመረውን የክትትል፣ የድጋፍ፣ የአሳታፊነት እና ቅንጅታዊ ስራ አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ሲሉ የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች ላስመዘገቡት መልካም ውጤት ሚኒስትር ዴዔታው አመስግነዋል፡፡
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ በበኩላቸው በሀገሪቱ ላይ የመጣውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ከጸጥታ ኃይላችን ጎን ለጎን በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ በማቋቋም ሂደት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አይተኬ ሚና የተጫወቱ መሆኑን አንስተው ባለሥልጣን መስሪያቤቱ ያቀረበላቸውን አገራዊ ጥሪ ተቀብለው ከ350 ሚሊየን ብር በላይ የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ በማሰባሰብ በጦርነቱ ለተጎዱ ዜጎች ማድረስ መቻሉን ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከጊዜ ወደጊዜ የአሠራር ስዓቱን በማዘመን ከ45 በላይ አገልግሎቶችን በኤሌክትሮኒክ ሰርቪስ በመስጠት ላይ ይገኛል ሲሉ በመግለጽ የተቋሙን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ለማጎልበት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ የምክክር መድረኮችን በማድረግ ወጥነት ያለው የአሠራር ስርዓት ለማጎልበት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
ሌላው ዋና ዳይሬክተሩ ያሱት ለዘመናት ስንናፍቀው የነበረው ታላቁ ህዳሴ ግድብ እውን ሆኖ የመጀመሪያ ምዕራፍ ተጠናቆ ኃይል ማመንጨት በጀመረበት ማግስት መሆኑና የዚህ ድል ባለቤት በመሆናችን እኳን ድስ ያለን ብለዋ፡፡ከሪፖርቱ በተጨማሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከባለሥልጣን መስሪያቤቱ ጋር በቀጣይ አብሮ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በዛሬው እለት የኢ-ሰርቪስ አገልግሎትን በይፋ ያስጀምራል፡፡