በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀና በተቋሙ ውስጥ የሚገኙ ሴክሬታሪዎች የተሳተፉበት Customer Handling and Office Management በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡
በሥልጠና መድረኩ ላይ ተገኝተው ሥልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት በፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እንዳልካቸው ወርቁ በሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን በሴክሬታሪነት የስራ ሙያ ላይ ለሚገኙ ሠራተኞች የባለ ጉዳይ አያያዝ እና የቢሮ አስተዳደርን አስመልክቶ ፀሐፊዎች የተቋሙን ገፅታ በመገንባት በኩል ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው መሆኑን እና የቤሮ ውስጥ አያያዝ ለውስጥም ሆነ ለውጭ ተገልጋይ የተመቸ እንዲሆን አድርጎ እንዴት መመራት ይኖርበታል በሚሉ ጉዳዮች ላይ የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ላቅ ያለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም ሰልጣኞቹ ያሉባቸውን ክፍተቶች እያዩ አቅማቸውን ማሳደግ መቻል እንደሚገባቸው ያወሱት ዳይሬክተሩ ለሁለት ቀናት የሚሰጠውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና በትኩረት በመከታተል በቀጣይነት የተቋሙን ዓላማና ግቦች በማሳካት ረገድ የሚጠበቅባቸውን አዎንታዊ አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚገባቸው በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡
በፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳሬክቶሬት በተለያየ ዘርፍ ሥልጠናዎችን በማዘጋጀትና ሰራተኞችን በማብቃት የተሻለ የስራ አቅም እንዲኖራቸው በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ይህንኑ መሠረት በማድረግ በዛሬው እለት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ የስራ ክፍሎች ለተወከሉ ከ40 በላይ ለሚሆኑ ሴክሬታሪዎች ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡
ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና በደንበኛ አያያዝ እና አገልግሎት አሰጣጥ፣ ከተገልጋይ የሚቀርብ ቅሬታ አቀባበል፣ የቢሮ ስራ አስካሀጅ አበይት ተግባራትና ኃላፊነት፣ በቢሮ ውስጥ መልካም የሆነ የእርስ በርስ ግንኙነት እና ተያያዥነት ባላቸው ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ በመስኩ ላይ የረጅም አመታት ልምድን ባካበቱ ባለሙያዎች የሚሰጥ ሥልጠና እንደሆነ ተጠቁሟዋል፡፡
በአጠቃላይ የተቋሙን ራዕይ፣ ዓላማና ግብ ለማሳካት ጉልህ ድርሻ ሊያበረክቱ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ መሰል ሥልጠናዎች መሰጠታቸው ሰልጣኞች የሠራተኛውን አቅም በማሳደግ ወቅቱ የሚፈልገውን አገልግሎት በተሟላ ሁኔታ መስጠት የሚያስችል አቅም እንደሚፈጥርላቸወ ተመልክቷል፡፡