በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ በግዳጅ መፈናቀል ላይ ያተኮረ የህግና ፖሊሲ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

A First-of-Its-Kind Legal and Policy Consultation Forum Focused on Forced Displacement is Underway

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር ብሔራዊ የፍልሰት ትብብር ጥምረት ጽ/ቤት፣ ከኢፌዴሪ ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከአለም የፍልሰት ድርጅት(IOM) ጋር በመተባበር የተዘጋጀና ትኩረቱን በግዳጅ መፈናቀል የሕግና ፖሊሲ፡ መልሶ ማቋቋምን በሚመለከት መፍትሄ ማፈላለጊያና በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የምክክር መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በግዳጅ የተፈናቀሉ ዜጎች ተወካዮች፣ ከኦሮሚያ እና ትግራይ ክልሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ጽ/ቤት ሀላፊዎችና ቡድን መሪዎች፣ በሱዳን የእርስ በርስ ግጭት ምክንያት ተፈናቅለው የተመለሱ ወገኖች ተወካዮች፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፍልሰት ትምህርት ክፍል ምሁራን እንዲሁም የተለያዩ ሀገራዊና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት በሚካሄደው መድረክ ላይ በመገኘት የእኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የብሔራዊ የፍልሰት ትብብር ጥምረት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብሀም አያሌው የግዳጅ ፍልሰት መደበኛ እና መደበኛ ባልሆነ ፍልሰት ውስጥ የሚካሄድ ሂደት ሆኖ በሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ በሆነ ምክንያት በመከሰት የሰው ልጆችን ለተለያዩ ችግርች የሚዳርግ ክስተት መሆኑን በመግለፅ በኢትዮጵያ ውስጥ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ መንገድ ከሚኖሩበት አካባቢ በግዳጅ ተፈናቅለው በችግር ውስጥ የሚኖሩ በርካታ ወገኖች ስለሚገኙ አስቸኳይ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ከመሆኑም በተጨማሪ በሰው መንገድና በህገ ወጥ መንገድ ሰዉን ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለሚፈፅሙ አካላት ተጋላጭ በመሆናቸው ጉዳዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

አቶ አብረሀም አያሌው አያይዘውም የግዳጅ ፍልሰት የሚያስከትለውን ዘርፈ ብዙ ችግር ለመፍታ ፖሊሲዎችን ከማዘጋጀት ጀምሮ የተለያዩ ተግባራት እየተካወኑ ቢሆንም ችግሩን ባለበት ሊያስቆሙት አለመቻሉን ጠቁመው፤ የሀገር ውስጥ ፍልሰትን ለመግታት የካምፓላ ስምምነትን መነሻ በማድረግ በ2012 ዓ.ም ፖሊሲ መዘጋጀቱን አስታውሰዋል፡፡

አያይዘውም ግጭቶች፣ የአየር ንብረት ለውጥ እንዲሁም በሰው መነገድ እና በህገወጥ መንገድ ሰውን ድንበር የማሻገር ወንጀል ፈፃሚ አካላት የግዳጅ መፈናቀልን እያባባሱት በመሆኑ ይሄንን ወንጀል ለመከላከል ሰዎችን ለሀገር ውስጥ ፍልሰት የሚዳርጉ አካላትን ለሕግ አቅርቦ ተጠያቂ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው ይህ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የምክክር መድረክ የግዳጅ ፍልሰት የሕግና ፖሊሲ የምክክር መድረክ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት የተሳተፉበት በመሆኑ በትኩረት መከታተልና ገንቢ የሆኑ ሀሳባንና አስተያየቶችን በመስጠት ለመፍትሄው አብሮ መሥራት ከተሳታፊዎች የሚጠበቅ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በመድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ከአለም የፍልሰት ድርጅት(IOM) ፍልሰት መከላከል ቢሮ ሀላፊ ሚስ ዲሞሪ በበኩላቸው ፍልሰትን ለመከላከልና ተመላሾችን ከህረተሰቡ ጋር መልሶ እንዲቀላቀሉ የማድረግ ስራው የተለያዩ አካላትን በማሳተፍ መቀጠሉን አስታውሰው፤ ይህ በግዳጅ መፈናቀል ላይ አተኩሮ የሚካሄደው የሕግና ፖሊሲ ምክክር በመፈናቀሉ ምክንያት የተከሰቱ ችግሮችን መሠረት አስይዞ ለመፍታት የሚያግዝ በመሆኑ በጋራ መሥራት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

በመቀጠል መድረኩ ላይ ተገኝጠው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ አሰልፈው አመዲን በበኩላቸው ከኦሮሚያና ትግራይ ክልሎች የተገኙ የፍልሰት ተመላሽ ማህበራት ተወካዮች እንዲሁም በሱዳን በተከሰተው የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት በግዳጅ ተፈናቅለው ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም የተዘጋጀ መድረክ በሰው የመነገድና በህገ ወጥ መንገድ ሰውን ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከል፣፤ ተጎጂዎችን አስፈላጊ የሆነ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ እንዲያገኙ የሚስችሉ ተግባራት በመከናወን ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

አያይዘውም ዜጎች በተለያዩ ምክንያቶች በግዳጅ የሚፈናቀሉበት ሁኔታ ሲኖር ተጋላጭነታቸውን ለይቶ ድጋፍ ማድረግ ስለሚገባ በዚሁም መሠረት ከሱዳን ተፈናቅለው ለተመለሱ ወገኖች ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት እንዲሁም ከማህበረሰቡ ጋር ተመልሰው በሚዋሀዱበት ሁኔታ ላይ የሕግና ፖሊሲ የምክክር መድረኩ ቀጣይ የሆኑ አቅጣጫዎችን ያመላክታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል፡፡

ይህ ለሁለት ቀናት የሚቆየው የግዳጅ መፈናቀል የሕግና ፖሊሲ የምክክር መድረክ አጠቃላይ የፍልሰት እንቅስቃሴ ሁኔታዎች እንዲሁም የግዳጅ መፈናቀል ሁኔታው የሚገኝበትን ደረጃ እና በቀጣይ መከናወን ስለሚገባቸው ተግባራትና ከመድረኩ በሚጠበቁ ውጤቶች ዙሪያ በማተኮር በባለሙያዎች የመነሻ ፅፎች ቀርበው ውይይት የሚደረግበት እንዲሁም ቀጣይ አቅጣጫ የሚቀመጥበት እንደሆነ ተመልቷል፡፡

Tagged Under: Cross-Border Crime displacement economic reintegration forced forced displacement framework Human Rights Violations Humanitarian Aid internal internal displacement international iom iom (international organization for migration) legal legal framework Migration organization oromia Policy refugee refugee resettlement repatriation Resettlement smuggling of migrants social reintegration Stakeholder Consultation Sudan Tigray
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች