የብሔራዊ እና ክልላዊ የፍልሰት የትብብር ጥምረቶች የ2015 ዓ/ም አፈጻጸም ግምገማ እና 2016 ዕቅድ ውይይት ተካሄደ

2015 Performance Review and 2016 Plan Discussion Held for National and Regional Migration Cooperation Coalitions

በመድረኩ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክበርት ወ/ሮ እጸገነት መንግስቱ፤ የፍትሕ ሚኒስቴር የመንግሥት ሕግና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስቴር ዲኤታ አቶ አለም አንተው አግው ፤ በፍትሕ ሚኒሰቴር የተቅላይ ዐ/ሕግ ዘርፍ ሚኒስቴር ዲኤታ አቶ ፍቃዱ ጸጋ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ሚኒስቴሮች ከፍተኛ ኃላፊዎች እና የሁሉም ክልሎች የፍትሕ ቢሮ ኃላፊዎች እና ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ተገኝተዋል

በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የኢጋድ ተወካይ አቶ ሙጂብ ጀማል ፍልሰት መብት ስለሆነ ሰብዓዊ መብትን በጠበቀ መልኩ እንዲሆን ውጤታማ የፍልሰት አስተዳደር እንዲኖር የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ኢጋድም የፍልሰት አስተዳደር ፖሊሲ አውጥቶ ከመንግሥት ጋር በመተባበር እና የሚከናወኑ ስራዎችን በመደገፍ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ በቀጣይም ይህንኑ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

አቶ አለም አንተ አግደው ባስተላለፉት ቁልፍ መልዕከትም መደበኛ በሆነ መንገድ ወደ ውጭ ሀገር የሚሄዱ ዜጎቻችን ከዕውቀት ሽግግር አንጸር እና ከሚላከው ገንዘብ ሀገራችን እየተጠቀመች እንደምትገኝ ነገር ግን መደበኛ ባልሆነ ፍልሰት ዜጎቻችን ከፍተኛ የመብት ጥሰት እንደተጋለጡ በተለይ ደግሞ መካከለኛው ምስራው ሀገራት መደበኛ ባልሆነ መንገድ እየሄዱ ያሉ ዜጎቻችን የበለጠ ተጋላጨጭ እንደሆኑ እንዲሁም በሀገር ውስጥ የሚካሄዱ በሰው መነገድ ወንጀል ለድንበር ተሻጋሪ የሰው መነገድ ወንጀል እና በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል መነሻ እየሆነ እና ጉዳቱም በዛው ልክ ከፍተኛ ስለሆነ ትኩረት መሰጠት እንዳለበት በተጨማሪም የትብብር ጥምረቶች እና የሚመለከታቸው ተቋማት እያከነናወኑ ባሉት ተግባራት አሜሪካ በምታወጣው ሪፖርት ከዚህ ቀደም ከነበረ ደረጃ ከፍ ብለን ደረጃ 2 ላይ መቀምጥ መቻላችንን ይህም ስራ ተጠነክሮ መቀጠል እንዳለበት በተለይ የፖለቲካ ቁርጠኝነት በማሳየት ካለንበት ችግር መውጣት እንደሚገባ ግልጸዋል፡፡

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ክብርት እጸገነት መንግስቱ በበኩላቸው የተወካይ ምክር ቤት የፍልሰትን ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ በዚህም የተለያዩ ህጎች መጽደቃቸውን ገልፀው የፍትሕ አካለት ወንጀል ፈጻሚዎችን ወደ ሕግ አቅርቦ የማያዳግም እርምጃ እንወሰድባቸው የሚያስችል ስራ መሥራት እንደሚገባቸው የተዛባና የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጩ ሚዲያዎችም የእርምት እርምጃ መውሰድ አንደሚገባቸው የውጭ ሀገር ስምሪትም በዜጎች ፍላጎት ልክ እንዲሆን የስራና ክህሎት ሚኒስተር ከፍተኛ ስራ እንደሚጠበቅበት እና ባጠቃለይ ማህበረሳባችን መደበኛ ያለሆነውን ፍልሰት አብዝቶ እንዲጠየፍ እና ወንጀል አድራጊዎችን አሳልፎ እንዲሰጥ መሥራት እንደሚያስፈልግ ብሎም ዜጎች በትክክለኛ መረጃ መሠረት ውሳኔ እንዲወስኑ ለማስቻል ከፍተኛ ስራ መሥራት እንደሚጠበቅ አሳስበዋል፡፡

የብሔራዊ እና የክልላዊ የትብብር ጥምረቶች የ2015 ዓ.ም አፈጻጸም ሪፖርት እና የብሔራዊ የትብብር ጥምረቱ የ2016 ዓ/ም ዕቅድ ከቀረበ በኃላም ውይይት ተካሂዷል፡፡

በማጠቃለያም ዕቅዱን ለማስፈጸም በትብብር እና በቅንጅት መሥራት እንደሚያስፈልግ፤ ወንጀል ምርመራን በተመለከተ ተጎጂዎች ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ በኃላ ማቆያ ማዕከላት ላይ ለረጅም ጊዜ ማቆየት ስለማይቻል ምርመራው ከመነሻው ሀገር መመርመር የሚቻልበትን ሁኔታ የውጭ ጉዳይ እያስተባበረ መሆኑን ለምሳሌ በሳውዲ አረቢያ ግብረሃይል ተልኮ የምርመራ ስራዎች እየተሰሩ ያሉ መሆኑን፤ ግንዛቤን ከመፍጠር አንጻር ሁሉም ተቋም እንደየተቋሙ ኃላፊነት ዕቅድ በማውጣት የሚሰራው ሆኖ የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳዩ ካለው ኃላፊነት አንጻር የማህበረሰባዊ አደረጃጀቶችን ጭምር በመጠቀም እንደሚሰራ፤ ከፍልሰት የሚገኙ ጥቅሞች ላይ በትኩረት መሥራት እንዳለብን ጉዳቶቹንም ለመከላከል በተጠናከረ መልኩ እየተሰሩ ያሉትን ስራዎች አጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግ፤ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን በሚመለከት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ይሄንንም አስመልክቶ በተለይ ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጥበቃ እና ከለላ ከማድረግ አንጻር ረቂቅ ሕግ ተዘጋጅቶ መፅደቅ ብቻ የቀረው በመሆኑ ሁሉም የሚመለከተው ተቋም በዚህ ልክ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንዳለበት ተገልጻል፡፡

Tagged Under: act Action Plan civil liberties decree fundamental rights Human Rights Human Trafficking igad Immigration internal displacement international International Cooperation international migration Justice law Law Enforcement legislation Migration Performance Review Police Policy proclamation Refugees Regional Cooperation Regulation saudi arabia Security Smuggling statute
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች