የተሻረ

የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝን እንደገና ለመደንገግ የወጣ አዋጅ

መሬት የመንግሥትና የሕዝብ ንብረት ሆኖ የመሬት አጠቃቀም በሕግ እንደሚወሰን በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት የተደነገገ በመሆኑ በተቻለ መጠን በመሪ ፕላን መሠረት የከተማ መሬት የመጠቀም መብትን ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሊዝ ዋነኛ የመሬት ይዞታ ሥሪት ሆኖ የቆየ በመሆኑ፤

መሬት ነክ ንብረት ሊኖረው የሚችለውን የሕይወት ዘመንና የልማት ሥራ ወጪ መመለሻ የጊዜ ወሰን፣ እንዲሁም የልማት ሥራውን ልዩ ባህሪ እና በመሪ ፕላን የሚወሰን የቦታ አጠቃቀምን መሠረት በማድረግ በነፃ ገበያ መርሆዎች መሠረት የከተማ ቦታን በተገቢ ዋጋ በሊዝ ማስተላለፍ አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ልማትን ለማሳካትና የከተሞች ልማት በቀጣይነት የሚጎለብትበት አቅም እንዲፈጠር ለማድረግ እንደሚረዳ ስለታመነበት

ከእነዚህ ሁኔታዎች በመነሳትም ሊዝ ብቸኛ የከተማ ቦታ ይዞታ ሥሪት እንዲሆን ምቹ ሁኔታ መፍጠርና በመሪ ፕላን መሠረት ለልማት ሥራ ታቅዶ ቦታ በሊዝ የሚፈቀድበትም ሆነ የሚያዝበት ሂደት የተቀላጠፈና ከመሰናክሎች የፀዳ እንዲሆን ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣

በአንፃሩ ደግሞ በዚህ ሂደት ሕጋዊ መብቴ ወይም ጥቅሜ ተነካብኝ የሚል ማንኛውም ሰው ጥያቄው የሚስተናገድበት ሥርዓት ግልጽና የተቀላጠፈ እንዲሆን ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፣

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ 2(ሀ) በተደነገገው መሠረት ይህ አዋጅ ታውጇል።

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 272/1994
ቀን: ግንቦት 06፥ 1994 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

አዋጅ ቁጥር 1338/2016

•

ሐምሌ 25፥ 2016 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1336/2016

•

ሐምሌ 4፥ 2016 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1308/2016

•

የካቲት 1፥ 2016 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1287/2015

•

መስከረም 4፥ 2016 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
ደንብ ቁጥር 533/2015

•

ሰኔ 15፥ 2015 ዓ.ም.
የተሻረ
አዋጅ ቁጥር 1278/2015

•

የካቲት 20፥ 2015 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1267/2014

•

መጋቢት 9፥ 2014 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1265/2014

•

ታህሳስ 24፥ 2014 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ