በዓለምም ሆነ በሀገራችን የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያው እየዘመነ ከመሄዱ አንፃር ሀገራችንን የሚመጥኑ የመገናኛ ብዙኃን ዘርፎችን ማበራከት አስፈላጊ ስለሆነ፤
በዓለም አቀፍ ደረጃ የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያው እያደገ በመሄዱ እና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትም ከህትመት ሚዲያው በተጨማሪ በልዩ ልዩ የመልቲ ሚዲያ አማራጮች ዘርፍ ቢሠማራ ውጤታማ ሊሆን ይችላል፤ ለሀገራችን መገናኛ ብዙኃንም ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል ተብሎ በመታመኑ፤
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ማቋቋሚያ አዋጅን ከድርጅቱ ዓላማና ተልዕኮ አንፃር የግዥ እና የፋይናንስ ሥርዓቱን ማሻሻል በማስፈለጉ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•
•
•
•