የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የፌዴሬሽን ምክር ቤት በ፭ኛ የፓርላማ ዘመን ፮ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ጥቅምት 28 ቀን 2ሺ13 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 62(9) እና በአዋጅ ቁጥር 359/1995 አንቀፅ 14/2/ለ/ መሠረት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት፤
በኢፌዲሪ መንግሥት እና በህወሃት መካከል ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እና ግጭትን ለማቆም በፕሪቶርያ ደቡብ አፍሪካ በተደረገው የሰላም ሥምምነት አንቀጽ 10(1) መሠረት አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋቋም በማስፈለጉ፤
በመሆኑም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡