በአገልግሎት ላይ

ለአራተኛው ምዕራፍ የሴፍቲኔት ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል ብድር ከዓለም ዐቀፍ የልማት ማኅበር ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅ

ለአራተኛው ምዕራፍ የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል 391 ሚሊዮን 900ሺ ኤስ.ዲ.አር (ሦስት መቶ ዘጠና አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሺህ ኤስ.ዲ.አር) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በዓለም ዐቀፍ የልማት ማኅበር መካከል እ.አ.አ ኦክቶበር 31 ቀን 2014 በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤

ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥር  21 ቀን 2007 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ያጸደቀው በመሆኑ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጃል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 884/2007
ቀን: የካቲት 16፥ 2007 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

አዋጅ ቁጥር 1301/2016

ታህሳስ 10፥ 2016 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ