ለሁለተኛው ምዕራፍ የዘላቂ መሬት አያያዝ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል የ107 ሚሊዮን 174 ሺ 255 (አንድ መቶ ሰባት ሚሊዮን አንድ መቶ ሰባ አራት ሺ ሁለት መቶ ሃምሳ አምስት) የአሜሪካን ዶላር ብድር የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ነሐሴ 2 ቀን 2014 ዓ.ም
በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህን ስምምነት የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም በአካሄደው 12ኛ መደበኛ ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡