የሴቶችን የንግድ ሥራ ፈጠራ ብቃት ለማሳደግ ለሚያስችለው ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል 32ሚሊዮን 200 ሺ ኤስ.ዲ.አር. (ሠላሳ ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺ ኤስ.ዲ.አር.) ብድር የሚያስገኘው የፋይናንስ ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል እ.አ.አ ጁን 12 ቀን 2012 በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሐምሌ 4 ቀን 2004 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•