ለመሠረታዊ አገልግሎቶች አሰጣጥ ድጋፍ ምዕራፍ ሁለት ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የሚውል 113 ሚሊዮን 700ሺ ኤስ.ዲ.አር. (አንድ መቶ አሥራ ሦስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሺ ኤስ.ዲ.አር.) በብድር እንዲሁም 161 ሚሊዮን 700ሺ ኤስ.ዲ.አር. (አንድ መቶ ስልሳ አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሺ ኤስ, ዲ. አር.) በዕርዳታ የሚያስገኘው የፋይናንስ ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል እ.ኤ.አ. ማርች 10 ቀን 2011 በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት መጋቢት 29 ቀን 2003 ዓ.ም ባካሔደው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•
•
•