ኢትዮጵያ ባላት የተለያየ የመልክዓ ምድር አቀማመጥና የአየር ንብረት ምክንያት ሰፊና የዳበረ የሕይወታዊ ሀብት ስብጥር የሚገኝባትና በዓለም ላይ ይህን መሰል ጸጋ ካላቸው አካባቢዎች አንዷ በመሆኗ፤
ይህ በዕዕዋት፣ በእንስሳትና በጥቃቅን ሕዋሳት የሚካተተው የሕይወታዊ ሀብቷ ለሀገሪቱ የግብርና፣ የኢንዱስትሪና የጤና ዘርፎች እድገት እንዲሁም ለሌሎች ማኅበራዊና ልማት ነክ ተግባራት ከፍተኛ ድርሻ ያለው መመኪያ የተፈጥሮ ሀብት በመሆኑ፤
የአየር ንብረት ለውጥ መከሰት ፣ የድርቅና ምድረ በዳነት መስፋፋት ፣ የሕዝብ ቁጥር ከልማት ዕድገት ጋር ባልተመጣጠነ ሁኔታ መጨመር እንዲሁም የሕይወታዊ ሀብት ጥበቃን ያላገናዘቡ የግብርናና የኢንዱስትሪ ቴክኖሎጂዎች ተግባራዊ መሆን ፣ ይህን ሀብት መልሶ ሊተካ በማይቻል ሁኔታ እያጠፉት በመሆናቸው በዚህ የተነሳ በተፈጥሮ ሀብት ላይ የሚደርሰው ጥፋት አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ፤
በኢትዮጵያ ያለውን ሕይወታዊ ሀብት በሚገባ ለመቃኘት፣ ለመሰብሰብ፣ ጠብቆ በዘላቂነት ለማቆየትና ተመራምሮ ጥቅም ላይ ለማዋል ሁኔታዎችን ማመቻቸት ቅድሚያ ትኩረት ሊሰጣቸው ከሚገባቸው ለልማት አስፈላጊ ከሆኑ ተግባራት አንዱ በመሆኑ፤
በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያ በሕይወታዊ ሀብቷ ላይ ያላትን ሉዓላዊ መብት ከማስከበር ጐን ለጐን ሀብቱ ከዜጐቿ አልፎ ተርፎ በየትኛውም ዓለም ለሚገኝ የሰው ዘር ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ በዓለም አቀፍ ውሎች መሠረት በሚገባ ለመጠበቅ ፣ ለመንከባከብና በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል የተስማማች በመሆኗ፤
የሕይወታዊ ሀብትን ጥበቃ ፣ ምርምርና አጠቃቀም በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚያከናውን ፣ የሚመራና የሚያስተባብር አካል ማዋቀር በማስፈለጉ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•
•
•
•
•
•