የኢትዮጵያ የዕፅዋት ዘር ዘርፍ የግብርና ምጣኔ ሃብት ዕድገትን፣ የውጭ ኢንቨስትመት ማበረታታትን፣ የውጭ ምንዛሬ ገቢ ማሳደግን፣ ከውጭ የሚገባ የግብርና ምርትን ሚዛናዊ በሆነ ንግድ እንዲመራ ማድረግ፣ የምግብ፣ ስነ-ምግብ እና የመኖ እንዲሁም የደን ውጤቶችን ዋስትና ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ፤
ዘላቂ የዕፅዋት ዘር ሥርዓት በመዘርጋት የዝርያ እና ዘር በብዛትና በጥራት ለአምራቾች እንዲቀርብ በማድረግ ሥርዓተ-ምህዳር ላይ የሚኖረውን አስተዋጽኦ ማሳደግ በማስፈለጉ፤
የግልና የመንግሰትን የዕፅዋት ዘር ኩባንያዎች በማሳተፍ እና ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነትን በማረጋገጥ ለምርምር፣ ለቴክኖሎጂ ሽግግርና ሥርፀት፣ ለምርትና ምርታማነት ዕድገትና ለምርት ጥራት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ በላቀ ደረጃ ማሳደግ በማስፈለጉ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•
•
•
•
•
•
•