የአካባቢ መራቆትንና የተፈጥሮ ሀብት መመናመንን በመከላከል፣ የብዝሀ ሕይወት ሀብትን በመጠበቅ፣ የውኃ ሀብትን በማጎልበትና የሙቀት አማቂ ጋዞችን ልቀት በመቀነስ የመሬት የማምረት አቅም ተጠብቆ ለመጪው ትውልድ እንዲተላለፍ እና በዚህም ለሰብልና ለእንስሳት ሃብት ልማት ሥራ ምቹ ሁኔታ መፍጠር በማስፈለጉ፤
የአርሶ አደሩ፣ አርብቶ አደሩ እና ከፊል አርብቶ አደሩ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር በማድረግ ለምግብ ዋስትና መረጋገጥና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ምቹ መደላድል ለመፍጠር ይቻል ዘንድ ቀደም ሲል የተጀመሩትን የተፋሰስ ልማት ሥራዎች ማስቀጠል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
ባለፉት ዓመታት የተከናወኑት የተፋሰስ ልማት ሥራዎች ከፍተኛ የሰው ጉልበትና የገንዘብ ወሬ ተደርጐባቸው እንዲለሙ የተደረገ ቢሆንም ዘላቂነታቸውን ለማረጋገጥ የተፋሰሱ ተጠቃሚዎች በባለቤትነት ስሜት ተረክበው የተፈጥሮ ሀብቶችን የሚያስተዳድሩበት የርክክብ፣ የአጠቃቀም፣ የአጠባበቅና የተጠያቂነት አሠራር ማስፈን ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ፤
የማህበረሰብ ተፋሰስ ተጠቃሚዎች ያለሙትን ሀብት ለማስተዳደር፣ ለመጠቀምና ለመጠበቀ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የሚችሉበትን ሁለንተናዊ አቅም ማሳደግ በማስፈለጉ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (2) (ሀ)መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•
•
•
•
•