ለመሠረታዊ አገልግሎት ማስፋፊያ ምዕራፍ 3 ፕሮጀክት ከፊል ማስፈፀሚያ የሚውል 8 ሚሊዮን ዮሮ (ስምንት ሚሊዮን ዮሮ) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በጣሊያን ሪፐብሊክ መንግስት መካከል እ.አ.አ ሴፕቴምበር 5 ቀን 2014 በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዚያ 22 ቀን 2007 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግስት አንቀፅ 55 (1) እና (12) መሰረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•