ለአዲስ አበባ የኃይል ማስተላለፊያ መረብ ማሻሻያ እና ደረጃውን ማሳደጊያ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል መጠኑ 1 ቢሊዮን 145 ሚሊዮን የቻይና ዩዋን (አንድ ቢሊዮን አንድ መቶ አርባ አምስት ሚሊዮን የቻይና ዩዋን) የሚያስገኘውን የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በቻይና ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ መካከል ሐምሌ 21 ቀን 2008 በቤጂንግ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታህሣሥ 18 ቀን 2009 ዓ.ም ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ያጸደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፦
•
•
•
•
•
•
•
•
•
•