በአገልግሎት ላይ

የሙስና ወንጀሎች አዋጅ

በ 1996 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ህግ የተደነገጉ የሙስና ወንጀሎች ውስጥ በአፈፃፀም ወቅት የተስተዋሌ ግልጽነት የሚጎድላቸውን ድንጋጌዎች ግልጽ ማድረግና ማሻሻል በማስፈለጉ፤

የሙስና ወንጀሎቹ ማካተት የነበረባቸውን ተመሳሳይ ተግባራት በተለይም ከህዝብ የተሰባሰበ ወይም ለህዝብ ተብሎ የተሰባሰበ ሀብት በሚያስተዳድሩ የግል ዘርፍ አካላት የሚፈፀሙ ተመሳሳይ ተግባራትን በአግባበ ያላካተቱ በመሆናቸው እነዚህኑ ማካተት በማስፈለጉ፤

ሀገራችን ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸው የተባበሩት መንግስታት የፀረ-ሙስና ኮንቬንሽን እና የአፍሪካ ሀብረት የሙስና መከላከያና መዋጊያ ኮንቬንሽን በግል ዘርፍ ተቋማት ውስጥ የሚፈፀሙ የጉቦኝነት፣ የምዝበራ እና ተመሳሳይ ተግባራት በሙስና ወንጀልነት መፈረጅ እንዳለባቸው በፈራሚ አገሮች ላይ ግዴታ የሚጥል በመሆኑ ሕጉን ከዚህ አኳያ ማሻሻል በማስፈለጉ፤

በተግባር የታዩ ችግሮችን በመፍታት የተሟላ የሀሣ ማዕቀፍ እንዲኖር ማድረግ የፀረ ሙስና ትግሉን ለማጠናከር እና ሀገራችን ያለባትን አህጉራዊና ዓለም እተፋዊ ግዴታ በአግባቡ እንድትወጣ ለማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

የሙስና ወንጀሎች በፈጣን ሁኔታ የመቀያየር ባህሪ ስላላቸው አጠቃላይ ወንጀሎችን በሚደነግገው የወንጀል ህግ (ኮድ) ውስጥ እንዲካተቱ ከማድረግ ይልቅ ራሱን በቻለ አዋጅ እንዲደነገጉ ማድረግ ተመራጭ ሆኖ በመገኘቱ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ-መንግስት አንቀጽ 55 (1) እና (5) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 881/2007
ቀን: መጋቢት 25፥ 2007 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

አዋጅ ቁጥር 1309/2016

ታኅሣሥ 12÷ 2016 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1279/2015

የካቲት 2፥ 2015 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
ደንብ ቁጥር 484/2013

ሐምሌ 9፥ 2013 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1259/2013

ሀምሌ 08፥ 2013 ዓ.ም.
አዋጅ ቁጥር 1209/2020

ሐምሌ 9፥ 2012 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1182/2012

መጋቢት 4፥ 2012 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1124/2011

መጋቢት 27፥ 2011 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ