ሰኔ 1 ቀን 1997 ዓ.ም በአዲስ አበባ፣ ከጥቅምት 22 እስከ ህዳር 1 እንዲሁም ከህዳር 4 እስከ ህዳር 7 1998 ዓ. በመንግሥት የተወሰደው እርምጃ ከሰብአዊ መብት አጠባበቅ አንፃር ያለውን ሁኔታ ማጣራት ተገቢ ስለሆነ፣
በሀገራችን እየተገነባ ያለው ሥርዓት የህግ የበ ላይነት የሰፈነበት እና ራሱን በራሱ እያረመ የሚሄድ በመሆኑ ተከስተው የነበሩ ሁኔታዎችን ማጣራትና አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ እንዲቻል ትክክለኛውን ሁኔታ ለምክር ቤቱ የሚያቀርብ ገለልተኛ አጣሪ ኮሚሽን ማቋቋም ለተጀመረው የሰላምና የዲሞክራሲ ግንባታ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•
•
•
•