የአፍሪካ ሕብረትን ማቋቋሚያ ስምምነት፣ ኢትዮጵያና የተቀሩት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አባል አገሮች እኤአ ጁላይ 11 ቀን 2ሺ ሎሜ ላይ ስለተፈራረሙ፣
ስምምነቱ በሥራ ላይ የሚውለው፣ ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት አባል አገሮች፣ ሁለት ሦስተኛው የስምምነቱ ማጽደቂያ ሰነዶቻቸውን ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ዘንድ ተቀማጭ ካደረጉበት ጀምሮ ከ፴ ቀናት በኋላ እንደሚሆን በስም ምነቱ ውስጥ የተመለከተ ስለሆነ፣
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት 29 ቀን 1993 ዓም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት ከዚህ እንደሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•
•
•