ለገጠር ከተሞች ኤሌክትሪክ ስርጭት ማስፈጸሚያ ፕሮጀክትየሚውል መጠኑ 37,670,000 (ሰላሣ ሰባት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሰባ ሺ) ዩኒትስ ኦፍ አካውንት የሆነ ገንዘብ የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በአፍሪካ ልማት ፈንድ መካከል እ·ኤ·አ ማርች 10 ቀን 2002 በአቢጃን የተፈረመ በመሆኑ፣
መሠረታዊ የኢኮኖሚ ዓለም አቀፍ ውሎች ተፈጻሚ ከመሆናቸው በፊት መፅደቅ ያለባቸው በመሆኑ፣
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥቅምት 1 ቀን 1995ዓም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፣
በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•