ለሁለተኛ የገጠር የኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮጀክት ከፊል ማስፈፀሚያ የሚውል መጠኑ 87,200,000 ሺህ ዩኒትስ ኦፍ አካውንት (ሰማንያ ሰባት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ) ዩኒትስ ኦፍ አካውንት የሆነ ገንዘብ የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በአፍሪካ ልማት ፈንድ መካከል እ.ኤ.አ. ጃንዋሪ 12 ቀን 2007 በቱኒዝ ከተማ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ግንቦት 30 ቀን 1999 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፤
በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 55(1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•