ለዓለምገና – ቡታጅራ መንገድ ማሻሻያ ፕሮጀክት ማስፈ ጸሚያ የሚውል መጠኑ ዩ·ኤ· 18ሚሊዮን 500ሺህ (አሥራ ስምንት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ዩኒትስ ኦፍ አካውንት) የሆነ ገንዘብ የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትየጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ እና በአፍሪካ ልማት ፈንድ መካከል እ·ኤ·አ ጁላይ 21 ቀን 1998 በአቢጃን የተፈረመ በመሆኑ፤
መሠረታዊ የኢኮኖሚ ዓለምአቀፍ ውሎች ተፈጻሚ ከመሆ ናቸው በፊት መጽደቅ ስላለባቸው ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህዳር 15 ቀን 1991 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ፤
በሕገመንግሥቱ አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (10) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•