ለሐዋሳ-አገረማርያም የመንገድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል መጠኑ 105 ሚሊዮን ዩኒትስ ኦፍ አካውንት (አንድ መቶ አምስት ሚሊዮን ዩኒትስ ኦፍ አካውንት) የሆነ ገንዘብ የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በአፍሪካ ልማት ፈንድ መካከል እ.አ.አ. ፌብርዋሪ 3 ቀን 2012 በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዝያ 30 ቀን 2004 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•