በአገልግሎት ላይ

በተደጋጋሚ የሚከሰተውን ድርቅ በዘላቂነት ለማስወገድ ለሚያስችለው ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል ብድር ከአፍሪካ ልማት ፈንድ ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምምነት ማፅደቂያ አዋጅ

በተደጋጋሚ የሚከሰተውን ድርቅ በዘላቂነት ለማስወገድ ለሚያስችለው ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል 30 ሚሊዮን ዩኒትስ ኦፍ አካውንት (ሰላሳ ሚሊዮን ዩኒትስ ኦፍ አካውንት) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በአፍሪካ ልማት ፈንድ መካከል እ.አ.አ. በፌብሩዋሪ 23 ቀን 2013 በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤

ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 18 ቀን 2003 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 800/2005
ቀን: ሐምሌ 8፥ 2005 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች